ሳላዲን ሰኢድ ይቅርታ ጠይቋል

የብሄራዊ ቡድናችን አምበል ሳላዲን አሲድ በግብፅ ሱፐር ካፕ አል አህሊ ከ ዛማሌክ ጋር ባደረጉት ጨዋታ ጉዳት ከደረሰበት በኋላ ለቀጣዮቹ 6 ሳምንታት በጉዳት ከሜዳ እንደሚርቅ ተረጋግጧል፡፡

የአል-አህሊ ፉትቦል ዳይሬክተር የሆኑት የቀድሞው የአህሊ ኮከብ ዋኢል ጎማ ከኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ለሳላዲን የጥሪ ደብዳቤ እንደደረሰው ያስታወቁ ሲሆን ተጫዋቹም በጉዳት ምክንያት ከብሄራዊ ቡድኑ ዝግጅት ውጪ በመሆኑ ማዘኑንና ለጨዋው ባለመድረሱ ይቅርታ መጠየቁን በአል-አህሊ በኩል ለፌዴሬሽኑ መግለፁን ዳይሬክተሩ ተናግረዋል፡፡

በተመሳሳይ የኡመድ ኡኩሪ ክለብ የሆነው ኢትሃድ አሌሳንድሪያ ለተጫዋቹ የጥሪ ደብዳቤ ከኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን መላኩን አረጋግጧል፡፡

ያጋሩ