ሳላዲን ጉዳት አጋጥሞታል

ሳላዲን ሰዒድ ጉዳት እንዳጋጠመው ከአልጄሪያ የሚወጡ መረጃዎች ጠቁመዋል፡፡ ሳላ ኢንፌክሽን እንዳጋጠመው የኤምሲ አልጀር የብድን ሃኪም ተናግረዋል፡፡ ሳላ በሳምንቱ አጋማሽ በጋጠመው ኢንፌክሽን ምክንያት ከቡድኑ ተለይቶ ብቻው ልምምድ ሲሰራ ቆይቷል፡፡
ባለፈው ሰኞ በአልጄርያ ቻምፒዮናት ናሽናል ኤምሲ አልጀር ዩኤስኤም ኤል-ሃራችን 1-0 ባሸነፈበት ጨዋታ በተጠባባቂ ወንበር ላይ ሆኖ ተመልክቷል፡፡ ለክለቡ ኤምሲ አልጀር በውድድር ዘመኑ ለ80 ደቂቃዎች ብቻ የተሰለፈው ሳላዲን ከሲሸልሱ ጨዋታ በኋላ ለክለቡ ምንም ጨዋታ ማድረግ አልቻለም፡፡ ሳላዲን በክለቡ የሚከፈለው 3 ሚልዮን የአልጄርያ ዲናር ወይም 27 ሺህ ዩሮ ወርሃዊ ደሞዝ ከሚያሳየው አቋም ጋር የሚመጣጠን አይደለም በሚል የክለቡ ደጋፊዎች ከወዲሁ ቅሬታቸውን አሰምተዋል፡፡ ነገር ግን የሳላዲን ጉዳት ደጋፊዎችን እንዳሳሰበ መረጃዎች ጠቁዋል፡፡
የኤምሲ አልጀር ሃኪም ሳላዲን ብድኑ ከዲአርቢ ታጅናንት ጋር ዛሬ ለሚያደርገው የሊግ ጨዋታ እንደሚደርስ ተስፋ አድርገዋል፡፡ ሳላዲን የኢትዮጵያ ብሄራዊ ብድን ላለበት የዓለም ዋንጫ ቅድመ ማጣሪ ጨዋታ አልተጠራም፡፡

ያጋሩ