ፋሲካ አስፋው አዳማ ከነማን ለመቀላቀል ከጫፍ ደርሷል

የቅዱስ ጊዮርጊስ የአማካይ ስፍራ ተጫዋች የሆነው ፋሲካ አስፋው በያዝነው ሳምንት ወደ አዳማ ከነማ ሊዛወር እንደሆነ ተነግሯል፡፡ ፋሲካ ኢትዮጵያ ቡናን ለቆ ፈረሰኞቹን ከተቀላቀለ በኃላ አንድ የውድድር ዘመን ያሳለፈ ሲሆን፤ በቂ የመሰለፍ ዕድል አለማግኘቱ በክረምቱ የዝውውር ገበያ ወደ ሌላ ክለብ እንደሚዛውር በስፋት ሲዘገብ ቆይቷል፡፡ ቅዱስ ጊዮርጊስ እና አዳማ ከነማ በተጫዋቹ ዝውውር ላይ ተስማምተዋል፡፡ አዳማ ለፋሲካ ቀሪ የአንድ ዓመት ውል ማፍረሻ የሚከፍለው የገንዘብ መጠን አልተገለፀም፡፡ ዝውውሩ በዚሁ ሳምንት የሚጠናቀቅ ይሆናል፡፡
ፋሲካ አስፋው በዝውውር ገበያው የአዳማ ከነማ 11ኛው ፈራሚ ይሆናል፡፡ ፋሲካ በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ለኢትዮጵያ ቡና፣ መከላከያ እና ቅዱስ ጊዮርጊስ ተጫውቷል፡፡ አዳማ ከነማ በካስትል ፕሪምየር ሊግ የመጀመሪያ ጨዋታ ቅዱስ ጊዮርጊስን የሚገጥም ይሆናል፡፡

ያጋሩ