የኢትዮጵያ አንደኛ ሊግ የ2011 የውድድር ዓመት ዛሬ ሐረር ላይ በሚደረግ አንድ ጨዋታ ጅማሮውን ያደርጋል።
በስድስት ምድቦች 63 ክለቦችን ያሳትፋል የተባለው የዘንድሮው ውድድር የዕጣ ማውጣት ስነ-ስርዓት ጥቅምት 24 መከናወኑ የሚታወስ ነው። ሆኖም የተሳታፊዎች ቁጥር በተለያዩ ምክንያቶች ሊቀንስ እንደሚችል ሲገለጽ ኢትዮሶማሌ ልዩ ፖሊስ፣ ካሊ ጅግጅጋ፣ ቴክኖ ሞባይል እና ቄራ አንበሳ የመሳተፋቸው ጉዳይ አጠራጣሪ የሆኑ ክለቦች ናቸው፡፡
ውድድሩ ዛሬ በሚደረግ አንድ ጨዋታ ሲጀመር በምድብ ሁለት ሐረር ላይ የአንድ ከተማ ክለቦች የሆኑት ሐረር ሲቲ እና ሐረር አባድር 09:00 ላይ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።
የዚህ ሳምንት ጨዋታዎች የሚከተሉት ናቸው ፡-
ምድብ 1
እሁድ ኅዳር 30 ቀን 2011
ወሊሶ ከተማ 9:00 ኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ
ሆለታ ከተማ 9:00 መቱ ከተማ
ቶሎ ቦሎ ከተማ 9:00 አምቦ ከተማ
ንስር ክለብ PP ሱሉልታ ከተማ
አሶሳ ከተማ PP ዱከም ከተማ
ምድብ 2
ቅዳሜ ኅዳር 29 ቀን 2011
ሐረር ሲቲ 9:00 ሐረር አባድር
እሁድ ኅዳር 30 ቀን 2011
ወንጂ ስኳር 9:00 መተሀራ ስኳር
ከዳባ አፋር 9:00 መቂ ከተማ
ሞጆ ከተማ 9:00 ባቱ ከተማ
አራፊ ቡድን – ቢሾፍቱ ከተማ
መርሐ ግብር ውስጥ ያልተካተቱ – ካሊ ጅግጅጋ እና ሶማሌ ልዩ ፖሊስ
ምድብ 3
እሁድ ኅዳር 30 ቀን 2011
አማራ ፖሊስ 7:00 ዳሞት ከተማ
መርሳ ከተማ 9:00 እንጅባራ ከተማ
ዳንግላ ከተማ 9:00 ጎጃም ደብረማርቆስ
ዳባት ከተማ 9:00 አምባ ጊዮርጊስ
የጁ ፍሬ ወልዲያ 8:00 ላስታ ላሊበላ
አራፊ ቡድን – ደባርቅ ከተማ
ምድብ 4
እሁድ ኅዳር 30 ቀን 2011
አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ 9:00 ቦሌ ክፍለ ከተማ
ቂርቆስ ክ/ከተማ 9:00 ጉለሌ ክ/ከተማ
ናኑ ሁርቡ 9:00 ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ
ልደታ ክ/ከተማ 9:00 ሰንዳፋ በኬ
ሰሎዳ አድዋ 9:00 ትግራይ ውሃ ስራ
ምድብ 5
እሁድ ኅዳር 30 ቀን 2011
አአ ውሃ እና ፍሳሽ 9:00 አራዳ ክፍለ ከተማ
ትግራይ ዋልታ ፖሊስ 9:00 ራያ አዘቦ
ለገጣፎ 01 PP አዲስ አበባ ፖሊስ
ቦሌ ገርጂ ማኅበረሰብ PP ሰ/ሸዋ ደ/ብርሀን
መርሐ ግብር ውስጥ ያልተካተቱ – ቴክኖ ባይል እና ቄራ አንበሳ
ምድብ 6
እሁድ ኅዳር 30 ቀን 2011
አንጋጫ ከተማ 9:00 አረካ ከተማ
ጎባ ከተማ 9:00 ሀዲያ ሌሞ
ጋሞ ጨንቻ 9:00 ጂንካ ከተማ
ቡሌ ሆራ 9:00 ሮቤ ከተማ
ኮንሶ ኒውዮርክ 9:00 ጎፋ ባሬንቼ
አራፊ ቡድን – አሰላ ከተማ