ሳላዲን ሰኢድ ከ4 ቀን በኋላ ወደ ልምምድ ይመለሳል

በጉዳት ላይ የሚገኘው የዋልያዎቹ አምበል ሳላዲን ሰኢድ ከ4 ቀናት በኋላ ወደ መደበኛ ልምምዱ እንደሚመለስ ክለቡ በድረ-ገፁ አስታውቋል፡፡

ሳላዲን በእግሩ ጡንቻዎች ላይ ከደረሰበት ጉዳት በኋላ በጂምናዝየም እና በግሉ ቀለል ያሉ ልምምዶች ሲያከናውን የቆየ ሲሆን በታቀደው ቀን መሰረት ከቡድኑ ጋር ልምምድ እንደሚጀምር የክለቡ ፊዝዮቴራፒስት ዶ/ር ካሊድ ሞሃመድ አረጋግጠዋል፡፡

ሳላዲን ሰኢድ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ ከማላዊ ብሄራዊ ቡድን ጋር የሚያደርጉት ጨዋታ ያመልጠዋል፡፡

Photo – ahlyegypt.com

ያጋሩ