ዋልያዎቹ ዛሬ ማሊን ያስተናግዳሉ

በአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ 3ኛ የምድብ ጨዋታ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን የማሊ አቻውን በአዲስ አበባ ስታድየም 10 ሰአት ላይ ያስተናግዳል፡፡

በእስካሁኑ የማጣርያ ጨዋታዎች በአልጄርያ በሜዳው ፣ ከሜዳው ውጪ ደግሞ በማላዊ የተሸነፈው የሚአትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን የማለፍ ተስፋውን ለማለምለም የግድ ይህንን ጨዋታ በድል መወጣት ይጠበቅበታል፡፡

የብሄራዊ ቡድኑን አሰልጣኝነት ከተረከቡ ጊዜ ጀምሮ አንድም ጨዋታ ማሸነፍ የተሳናቸው ማርያኖ ባሬቶ ቶክ ጄምስ ፣ ሳላዲን ሰኢድ እና አስራት መገርሳን በጉዳት ሲያጡ በሁለቱ የማጣርያ ጨዋታዎች የተጠቀሙባቸው አሉላ ግርማና አዳነ ግርማን ቀንሰዋል፡፡ በተጎዱት እና በተቀነሱት ምትክም በተከላካይ ቢያድግልኝ ኤልያስ ወይም ዋሊድ አታ ፣ በቀኝ ተካላካይ ዴቪድ በሻ ወይም አንዳርጋቸው ይሳቅ ፣ አጥቂ ስፍራ ጌታነህ ከበደ እና የሱፍ ሳላህ በቋሚ አሰላለፍ ውስጥ ይካተታሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

የዛሬውን ጨዋታ ቱኒዚያዊው ሜድ ሰኢድ ኮርዲ በመሃል ዳኝነት ይመሩታል፡፡

ያጋሩ