የኮንፌዴሬሽን ዋንጫው አንደኛ ዙር የመክፈቻ ጨዋታን ኢትዮጵያውያን ይመሩታል

የካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ የመጀመርያ ዙር ጨዋታዎች ዛሬ በሚደረጉ ሁለት ጨዋታዎች ሲጀመሩ በላይ ታደሰ እና ኢትዮጵያውያን ረዳቶቹ ኪንሳሻ ላይ የሚደረግ ጨዋታ ይመራሉ። 

የኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፑብሊኩ ኤኤስ ንዩኪ እና የአንጎላው ፔትሮ ሎዋንዳ የሚያደርጉት የመጀመርያ ጨዋታ ዛሬ 10:30 ላይ በኪንሳሻው ስታዴ ማርቲይሪስ ሲከናወን ኢንተርናሽናል አርቢቴር በላይ ታደሰ በመሐል ዳኝነት ይመራዋል። ተመስገን ሳሙኤል እና ትግል ግዛው ደግሞ በረዳት ዳኝነት አብረውት እንዲመሩ በካፍ ተመድበዋል።

በላይ በቅድመ ማጣርያው የደቡብ ሱዳኑ አል ሒላል ጁባ እና የሊቢያው አል ናስር ጨዋታን በአራተኛ ዳኝነት ተመድቦ የነበረ ሲሆን በዚህ የውድድር ዘመን ለመጀመርያ ጊዜ በመሐል ዳኝነት የሚመራ ይሆናል። ተመስገን ሳሙኤል አንድ፣ ትግል ግዛው ደግሞ ሁለት የዘንድሮው የቻምፒየንስ ሊግ ቅድመ ማጣርያዎች ላይ በረዳት ዳኝነት መርተዋል።

ያጋሩ