ቻምፒየንስ ሊግ | አል አህሊን የሚገጥሙት የጅማ አባጅፋር የመጀመርያ ተሰላፊዎች ታወቁ

በካፍ ቻምፒየንስ ሊግ የአንደኛ ዙር የመጀመርያ ጨዋታ የግብፁን አል አህሊን የሚገጥመው ጅማ አባ ጅፋር የመጀመርያ 11 ተጫዋቾች ታውቀዋል። አሰልጣኝ ዘማርያም ወልደጊዮርጊስ በዛሬው ስብስባቸው ባሳለፍነው ሳምንት ከስሑል ሽረ ጋር ያለ ግብ አቻ ሲለያዩ ከተጠቀሙበት ቡድን መካከል ኄኖክ ገምቴሳን በአክሊሉ ዋለልኝ፣ ቢስማርክ አፒያህን በማማዱ ሲዴቤ፣ አስቻለው ግርማን በኤርሚያስ ኃይሉ ምትክ ወደ መጀመርያ አሰላለፍ መልሰዋቸዋል።


የጅማ አባ ጅፋር አሰላለፍ ይህንን ይመስላል፡-

ዳንኤል አጄይ

ዐወት ገብረሚካኤል – ከድር ኸይረዲን – አዳማ ሲሶኮ – ኤልያስ አታሮ

ይሁን እንደሻው – መስዑድ መሐመድ – ኄኖክ ገምቴሳ

አስቻለው ግርማ – ቢስማርክ አፒያ – ዲዲዬ ለብሪ


ጨዋታው ምሽት 1 ሰዓት በአሌክሳንድሪያ ሲደረግ በአል አህሊ ቲቪ የቀጥታ ስርጭት ሽፋን ያገኛል።

ያጋሩ