የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን የ2008 ካስቴል ፕሪሚየር ሊግ ፕሮግራምን ባለፈው መስከረም 21 ቢያወጣም የጨዋታዎቹን ቀን እና ሰአታት ሳያሳውቅ ቆይቶ ዛሬ የአንደኛውን ዙር 91 ጨዋታዎች ቀን እና ሰአት ይፋ አድርጓል፡፡

ፌዴሬሽኑ ዛሬ ይፋ ባደረገው የውድድር ካሌንደር መሰረት የአንደኛው ዙር ፕሮግራም ረቡእ ጥቅምት 17 ቀን 2008 በ9፡00 ኤሌክትሪክ ከመከላከያ አዲስ አበባ ስታድየም ላይ በሚያደርጉት ጨዋታ የሚጀመር ሲሆን አንደኛው ዙር መጋቢት 3 ቀን 2008 በ11፡30 በአዲስ አበባ ስታድየም መከላከያ አዳማ ከነማን በሚያስተናግድበት ጨዋታ ይጠናቀቃል፡፡

የአንደኛው ሳምንት ፕሮግራም

 

ረቡእ ጥቅምት 17 ቀን 2008

09፡00 – ኤሌክትሪክ ከ መከላከያ (አዲስ አበባ ስታድየም)

11፡30 – ደደቢት ከ ወላይታ ድቻ (አዲስ አበባ ስታድየም)

 

ሀሙስ ጥቅምት 18 ቀን 2008

09፡00 – አዳማ ከነማ ከ ቅዱስ ጊዮርጊስ (አዳማ አበበ ቢቂላ ስታድየም)

09፡00 – ሀዋሳ ከነማ ከ ሲዳማ ቡና (ሀዋሳ ስታድየም)

09፡00 – አርባምንጭ ከ ሀዲያ ሆሳእና (አርባምንጭ ስታድየም)

09፡00 – ዳሽን ቢራ ከ ድሬዳዋ ከነማ (ፋሲለደስ ስታድየም)

11፡30 – ኢትዮጵያ ቡና ከ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ (አዲስ አበባ ስታድየም)

 

ተጠባቂ ጨዋታዎች

1ኛ ሳምንት – ሀዋሳ ከነማ ከ ሲዳማ ቡና (ጥቅምት 18 በሀዋሳ ስታድየም)

2ኛ ሳምንት – ወላይታ ድቻ ከ አርባምንጭ ከነማ (ጥቅምት 22 በቦዲቲ ስታድየም)

5ኛ ሳምንት – ሲዳማ ቡና ከ ወላይታ ድቻ (ታህሳስ 11 በይርጋለም ስታድየም)

5ኛ ሳምንት – ኢትዮጵያ ቡና ከቅዱስ ጊዮርጊስ (ታህሳስ 12 በአዲስ አበባ ስታድየም)

6ኛ ሳምንት – ኢትዮጵያ ቡና ከ ደደቢት (ታህሳስ 16 በአዲስ አበባ ስታድየም)

7ኛ ሳምንት – ደደቢት ከ ቅዱስ ጊዮርጊስ (ታህሳስ 21 በአዲስ አበባ ስታድየም)

12ኛ ሳምንት – ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ መከላከያ (የካቲት 26 በአዲስ አበባ ስታድየም)

 

ማስታወሻ – የአንደኛውን ዙር ሙሉ ፕሮግራም በቀጣይ እንገልፅላችኋለን፡፡

ያጋሩ