አመሻሽ ላይ መከላከያ እና አዳማ ከተማን ያገናኘው የሊጉ ዘጠነኛ ሳምንት ጨዋታ በእንግዶቹ 5-1 አሸናፊነት ከተጠናቀቀ በኋላ የቡድኖቹ አሰልጣኞች ስለጨዋታው ያላቸውን አስተያየት እንዲህ ሲሉ ሰጥተዋል።
ሲሳይ አብርሃም -አዳማ ከተማ
” በውጤቱ በጣም ደስ ተሰኝቻለሁ ፤ አዳማ ከዚህ ቀደም በተለይ ዘንድሮ አጀማመራችን ጥሩ አልነበረም። ለዛም የዛሬው ጨዋታ እንደ ዋንጫ ጨዋታ ተመልክተን ለማሸነፍ ወደ ሜዳ ገብተናል። የጎሉን መጠን ነው እንጂ ያልገመትነው ለማሸነፍ ነበር የመጣነው ፤ እሱም ተሳክቷል፡፡ ችግሮቻችን ላይ ሰርተን ቀርበናል ዋናው የቡድናችን ችግር የነበረው የሥነልቡና ጉዳዮች እና የአጨራረስ ችግር ላይ በደንብ እየሰራን እንገኛለን፡፡ ”
ሥዩም ከበደ – መከላከያ
” በአጠቃላይ በእኛ በኩል እጅግ እጅግ ደካማ ነበርን ፤ በመጀመሪያው አጋማሽ የመጨረሻ ደቂቃዎች በተወሰነ መልኩ ለመነሳት ሞክረን ነበር። በሁለተኛው አጋማሽ በተለይ ሁለቱ ቀይ ካርዶች በአጠቃላይ የቡድኑን መንፈስ ገድለውታል፡፡ሁለት ሰው ከሜዳ ማጣታችን ለአዳማዎች ከፍተኛ መነሳሳት ፈጥሮላቸዋል ፤ በእርግጥ አዳማዎች በመጀመሪያው አጋማሽም የተሻሉ ነበሩ፡፡ በሁለተኛው አጋማሽ በተለይ የእኛ ከሥነ ምግባር ውጪ የሆኑ እንቅስቃሴዎች በተለይም የተመስገን ገብረኪዳን ድርጊት ውጤቱ ላይ ተፅዕኖ ፈጥሯል ፤ ክለቡም በራሱ ህገ ደንብ መሠረት እርምጃ የሚወስድበት ይሆናል፡፡”