የተስተካካይ ጨዋታዎች መርሀ ግብር ይፋ ሆኗል

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በይደር የተያዙት የሊጉ ጨዋታዎች መቼ እንደሚደረጉ አሳውቋል።

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ከአንደኛው እና ሰባተኛው ሳምንት ውጪ በሁሉም የጨዋታ ሳምንታት ለሌላ ጊዜ የተላለፉ ጨዋታዎች እንዳሉበት ይታወቃል። በተለያዩ ምክንያቶች ያልተደረጉት እነዚህ ጨዋታዎች እና የጅማ አባ ጅፋርን የአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ጨዋታዎች ተከትሎ በቀጣዮቹ ሁለት ሳምንታትም የማይካሄዱትን ሁለት ጨዋታዎች ጨምሮ 13 ጨዋታዎች በቀጣይ ጊዜያት የሚደረጉ ይሆናል። በዚህም ምክንያት የሊጉ አንደኛ ዙር መደበኛ መርሐ ግብር የካቲት 4 ቢጠናቀቅም የተስተካካዮቹ ጨዋታዎች እስከ የካቲት መጨረሻ ይደረጋል።

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስራ ሦስቱ ጨዋታዎች የሚካሄዱባቸው ቀናት እንደሚከተለው አሳውቋል።

2ኛ ሳምንት
ረቡዕ ጥር 29 ቀን 2011
አዳማ ከተማ 09:00 ቅዱስ ጊዮርጊስ
ወላይታ ድቻ 11:00
(አአ)
ሲዳማ ቡና
ሐሙስ ጥር 30 ቀን 2011
ባህር ዳር ከተማ 09:00 ስሑል ሽረ
ረቡዕ የካቲት 13 ቀን 2011
ጅማ አባ ጅፋር 09:00 መከላከያ
3ኛ ሳምንት
ሐሙስ ጥር 30 ቀን 2011
መቐለ 70 እ. 09:00 ፋሲል ከነማ
ቅዳሜ የካቲት 9 ቀን 2011
መከላከያ 10:00 ድሬዳዋ ከተማ
4ኛ ሳምንት
ረቡዕ ጥር 29 ቀን 2011
ደደቢት 09:00 መከላከያ
ሐሙስ ጥር 30 ቀን 2011
ጅማ አባ ጅፋር 09:00 ድሬዳዋ ከተማ
5ኛ ሳምንት
እሁድ የካቲት 10 ቀን 2011
መቐለ 70 እ. 09:00 ባህር ዳር ከተማ
6ኛ ሳምንት
ቅዳሜ የካቲት 9 ቀን 2011
ጅማ አባ ጅፋር 09:00 ደደቢት
8ኛ ሳምንት
ረቡዕ ጥር 8 ቀን 2011
ፋሲል ከነማ 09:00 ደደቢት
10ኛ ሳምንት
እሁድ የካቲት 17 ቀን 2011
ጅማ አባ ጅፋር 09:00 ፋሲል ከነማ
11ኛ ሳምንት
ሐሙስ የካቲት 21 ቀን 2011
መቐለ 70 እ. 09:00 ጅማ አባ ጅፋር

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *