በላይ ታደሰ ከኢትዮጵያውያን ረዳቶቹ ጋር ወደ ደቡብ አፍሪካ ያመራል

በካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ሁለተኛ ዙር የመልስ ጨዋታ ካይዘር ቺፍስ ከ ዜስኮ ዩናይትድ የሚያደርጉትን ጨዋታ ኢትዮጵያውያን ዳኞች ይመሩታል።

ቅዳሜ ጥር 11 በጆሀንስበርጉ ኤፍኤንቢ ስታድየም የሚደረገውን ጨዋታ በላይ ታደሰ በመሐል ዳኝነት የሚመራው ሲሆን ተመስገነረ ሳሙኤል እና ኃይለራጉኤል ወልዳይ በረዳት ዳኝነት አብረው እንዲመሩ በካፍ የተመደቡ ናቸው።

በላይ ታደሰ በመድረኩ የዲ.ሪ. ኮንጎው ኒዩኪ እና የአንጎላው ፔትሮ ሉዋንዳን የመጀመርያ ዙር ጨዋታ ከመራ በኋላ ሁለተኛውን ጨተታ የሚዳኝ ሲሆን በወቅቱ ተመስገን ሳሙኤል አብሮት በረዳትነት መምራቱ የሚታወስ ነው።

በሁለቱ ቡድኖች የመጀመርያ ጨዋታ የዛምቢያው ዜስኮ 3-1 በሆነ ውጤት ያሸነፈ ሲሆን ካይዘር ቺፍስ ውጤቱን ቀልብሶ ወደ ምድብ ዙር ለመግባት ከባድ ፈተና ይጠብቀዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *