የከፍተኛ ሊግ አጫጭር መረጃዎች

የክለቦች ቅሬታ 

በስድስተኛው ሳምንት የምድብ ለ ጨዋታ ሀላባ ከኢትዮጽያ መድን በነበረው ጨዋታ በ76ኛው ደቂቃ ላይ ከደጋፊ በተወረወረ ድንጋይ የዕለቱ ዋና ዳኛ ላይ ኤፍሬም ደበሌ ላይ ጉዳት ደርሶ ጨዋታው መቋረጡ የሚታወስ ነው። ይህን ተከትሎ የእግር ኳስ ፌዴሬሽን ዲሲፕሊን ኮሜቴ  በሀላባ ከተማ ላይ በጥር 10 ባሳለፈው ውሳኔ ጨዋታው በፎርፌ ለመድን እንዲሰጥ፣ ሁለት የሜዳው ጨዋታዎችን ከ200 ኪ/ሜ ርቀት በላይ ባለ ሜዳ እንዲጫወት እንዲሁም የገንዘብ ቅጣት እንዲከፍል እና የህክምና ወጪ እንዲሸፍን ወስኗል። ውሳኔን በተመለከተ ሀላባ ከተማ ይግባኝ የጠየቀ ሲሆን የሀላባ ውሳኔ የሰሙ የምድብ ለ ተፎካካሪ ቡድኖች የሆኑት ወልቂጤ ከተማ፣ ኢኮስኮ እና ሀምበሪቾ በውሳኔው ቅር መሰኘታቸውን በተለይ በምድቡ በነጥብ ተከታይ የሆኑት ቡድኖች ላይ ተፅዕኖ የሚፈጥር ውሳኔ ነው በማለት ለሶከር ኢትዮጵያ ገልፀዋል። የዲሲፕሊን መመሪያው አንቀፅ 69/7(መ) ላይ የሰፈረውን መመርያ የሚጥስ ነው የሚል ቅሬታም አሰምተዋል። 

የሀምበሪቾ እና ወልቂጤ ቅሬታ ደብዳቤ ይህን ይመስላል:-

ሀላባ ከተማ ከሜዳው ውጪ ይጫወታል

የይግባኝ ሰሚ ኮሚቴ በሀላባ ጉዳይ ላይ ምንም መልስ ባለመስጠቱ ምክንያት በዲስፕሊን ኮሚቴ ውሳኔ ተራ ቁጥር 3 ላይ የሰፈረው <<በሜዳው የሚያደርገውን ሁለት ጨዋታ ከ200 ኪ/ሜ ርቀት በሚገኝ ሜዳ እንዲያደርግ>> የሚለው ውሳኔ በዚህ ሳምንት ተግባራዊ ይሆናል። በዚህም መሰረት ሀላባ ከተማ ከአዲስ አበባ የሚደርገው ጨዋታ እሁድ በ9:00 በዲላ ስታዲየም ይደረጋል:: 

አቀባበል

ወደ አክሱም የሚያመራው ወልዲያ ደማቅ አቀባበል እንደሚደረግለት የአክሱም ከተማ ስራ አስኪያጅ ለሶከር ኢትዮጵያ ገልጸዋል። “የሁለቱ ክልል ቡድኖች በእግር ኳስ አማካኝነት ይበልጥ መቀራረብ አለባቸው። እግር ኳስ የሰላም ተምሳሌት ነው። በደጋፊዋቻችን ላይ ስፖርታዊ ጨዋነት ላይ ሰርተናል። በመቀጠልም የወልዲያን ቡድን በመኪናም ሆነ በአውሮፕላን የሚመጣውን ለመቀበል ዝግጅት አድርገናል። ይህንን ደሞ ባለፈው ላይ ደሴ ከተማን ተቀብለን አሳይተናል። በሰላም ነው ያለቀው። ውጤቱ ምን ሆነ ምን በፀጋ መቀበል ነው ያለብን። የኛ ፍላጎት ሰላም እና ሰላም ነው። ” ሲሉ ስራ አስኪያጁ አቶ ክንፈ ገልጸዋል።

ስፖርታዊ ጨዋነት

የኢትዮጽያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የከፍተኛ ሊግ ኮሚቴ በስፖርታዊ ጨዋነት ዙሪያ ስራውን አጠንክሮ እየሰራ እንዳለ ገለፀ። በተለይም ከዚህ ቀደም እርስ በርስ ሲገናኙ የስፖርታዊ ጉድለት የሚታይባቸውን ቡድኖች ላይ ትኩረት አድርጎ ስብሰባ በማድረግ ወደ ጋራ መስማማት እያመጣ መሁኑን ኮሚቴው ገልጿል። የጅማ አባ ቡና እና የቡታጅራ ጨዋታ አምና በሁለቱም መርሐ ግብር  የስፖርታዊ ጨዋነት ጉድለት የታየበት የነበር ሲሆን የሁለቱም የቡድን ባለድርሻ አካላት በአንድ ላይ በመስብሰብ ችግሩ መፍታት ችለዋል ተብሏል። የከፍተኛ ሊግ ኮሜቴ በቀጣይም ተመሳሳይ ስራዎችን በሁሉም ቡድኖች ላይ እንደሚሰሩ የኮሚቴው ሰብሳቢ አቶ ኢብራሂም አህመድ ለሶከር ኢትዮጽያ ገልፀዋል።

ደሴ ከተማ 

ከዋና አሰልጣኙ ኃይለየሱስ ጋር ከሳምንት በፊት የተለያየው ደሴ ከተማ በጊዜያዊነት በምክትል አሰልጣኙ ብርሀኑ ተፈራ እንደሚመራ ታውቋል። በቀጣይ 15 ቀናት ውስጥ የአዲስ አሰልጣኝ ቅጥር እንደሚፈፅሙም ከክለቡ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። 

ስምንተኛ ሳምንት 

ከፍተኛ ሊጉ ከአንድ ሳምንት እረፍት በኋላ ወደ ውድድር ሲመለስ ሁሉም የ8ኛ ሳምንት ጨዋታዎች እንደሚደረጉ ይጠበቃል። 

ምድብ ሀ

እሁድ ጥር 19 ቀን 2011

አውስኮድ 9:00 ወሎ ኮምበልቻ

አክሱም 9:00 ወልዲያ

ፌዴራል ፖሊስ 9:00 ለገጣፎ

ኢትዮ ኤሌክትሪክ 9:00 ደሴ ከተማ

ሰበታ ከተማ 9:00 ቡራዩ ከተማ

አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከ 9:00 ገላን ከተማ

ምድብ ለ

ቅዳሜ ጥር 18 ቀን 2011

ድሬዳዋ ፖሊስ 4:00 ወልቂጤ ከተማ

ዲላ ከተማ 9:00 ነገሌ አርሲ

እሁድ ጥር 19 ቀን 2011

ናሽናል ሴሚንት 4:00 ኢትዮጵያ መድን

ሀላባ ከተማ 9:00 አዲስ አበባ ከተማ

ኢኮስኮ 9:00 የካ ክ/ከተማ

ሰኞ ጥር 20 ቀን 2011

ሀምበሪቾ 9:00 ወላይታ ሶዶ

ምድብ ሐ

እሁድ ጥር 19 ቀን 2011

ካፋ ቡና 9:00 ቤንጅ ማጂ ቡና

ቡታጅራ ከተማ 9:00 ስልጤ ወራቤ

ሻሸመኔ ከተማ 9:00 ጅማ አባ ቡና

ነጌሌ ቦረና 9:00 አርባምንጭ ከተማ

ነቀምት 9:00 ከንባታ ሺንሺቾ

ሀድያ ሆሳዕና 9:00 ቢሾፍቱ አውቶ.

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *