የአማራ ዋንጫ ግማሽ ፍፃሜ ጨዋታዎች ነገ ይካሄዳሉ

በ12 የከፍተኛ ሊግ እና የብሄራዊ ሊግ ክለቦች መካከል በባህርዳር ከተማ ሲካሄድ የቆየው የአማራ ዋንጫ ነገ በሚደረጉ የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታዎች ይቀጥላል፡፡

በ3 ምድብ ተከፍሎ ሲካሄድ በሰነበተው ውድድር ፋሲል ከነማ ፣ አማራ ውሃ ስራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት (አውስኮድ) እና ባህርዳር ከነማ ከየምድባቸው 1ኛ በመውጣት ለግማሽ ፍፃሜ የደረሱ ሲሆን ሰሜን ሸዋ ደብረብርሃን ጥሩ 2ኛ በመሆን ቀሪዋን የግማሽ ፍፃሜ ቦታ አግኝቷል፡፡

የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታዎች ነገ የሚደረጉ ሲሆን በ8፡00 ፋሲል ከነማ ከ አውስኮድ ፤ በ10፡00 ደግሞ ሰሜን ሸዋ ደብረብርሃን ከ ባህርዳር ከነማ ይጫወታሉ፡፡ ሁለቱም ጨዋታዎች በባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ስታድየም ይደረጋሉ፡፡

ጥቅምት 25 የተጀመረው የአማራ ዋንጫ በመጪው እሁድ ህዳር 5 ቀን 2008 ይጠናቀቃል፡፡

ያጋሩ