ሲዳማ ቡና የጋና ዜግነት ያለው የተከላካይ አማካይ አልሀሰን ኑሁን አስፈርሟል፡፡
በፕሪምየር ሊጉ ውጤታማ ግስጋሴን እያደረገ ያለው የአሰልጣኝ ዘርዓይ ሙሉ ሲዳማ ቡና ያለበትን የተከላካይ አማካይ ቦታ ክፍተትን ለመድፈን በማሰብ በውጪ ተጫዋቾች የዝውውር መስኮቱ በማስመጣት ከ20 ቀናት በላይ በሙከራ ሲመለከተው የነበረው አልሀሰን ኑሁን በአንድ ዓመት የውል ኮንትራት አስፈርሟል፡፡
ወደ ሞልዶቫ አምርቶ ለሸሪፍ ቲራስፖል ከመጫወቱ ውጪ አብዛኛዎቹን የእግር ኳስ ህይወቱን በጋና ክለቦች ያሳለፈው የ26 ዓመቱ አልሀሰን ለጋናዎቹ ሪል ስፖርቲቭ፣ አሻንቲ ጎልድ እና ከ2017 ጀምሮ ደግሞ ለኢዱቢያስ ዩናይትድ ሲጫወት ቆይቷል።
አልሀሰን በሁለተኛው ዙር ለሲዳማ ቡና መጫወት የሚጀምር ሲሆን ከዮሴፍ ዮሀንስ እና ዘንድሮ ከመደበኛ የተከላካይ ስፍራው ወደ አማካይነት ተለውጦ በመሰለፍ ላይ ከሚገኘው ግርማ በቀለ ጋር የቋሚነትን ቦታ ለማግኘት ፉክክር ይጠብቀዋል፡፡
© ሶከር ኢትዮጵያ
በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡