‹‹ አሸንፈን እንመለሳለን ›› የኮንጎ አሰልጣኝ ክሎድ ለርዋ (በተለይ ለሶከር ኢትዮጵያ)

 

ለአለም ዋንጫ ማጣርያ ኢትዮጵያን ለመግጠም አዲስ አበባ የሚገኙት የሪፑብሊክ ኦፍ ኮንጎ አሰልጣኝ ክሎድ ለርዋ ለሶከር ኢትዮጵያ በሰጡት አስተያየት በፈታኝ ወቅት ላይ ቢገኙም አሸንፈን እንደሚመለሱ ተናግረዋል፡፡

 

ጥያቄ – ዝግጅቱ እንዴት ነበር?

መልስ – ዝጅግታችን በችግር የተሞላ ነበር፡፡ አምበላችን ኦኛንጌ እና ወሳኝ ተጫዋቻችን ፍሬቦሬ ዶሬ ተጎድተውብናል፡፡ ፌሬቦሬ በማጣርያ ጨዋታ ጊኒቢሳው ላይ 4 ግቦችን አስቆጥሮልን ነበር፡፡ ሌሎቹም ወሳኝ ተጫዋቾች ተጎድተውበናል፡፡ ለብሄራዊ ቡድን ተጫዋቾች በጉዳት እና ቅጣት ምክንያት ላይጫወቱ ይችላሉ፡፡ ይህ እግርኳስ ፀባይ ነው፡፡

ቲቪዬ ባፎውማ
ቲቪዬ ባፎውማ

ጥያቄ – ቲዬቫ ቢፉማ ከጉዳቱ አገግሞ ለጨዋታው ይደርሳል?

መልስ – ቲዬቫን ቢፉማ ከጉዳቱ አገግሟል፡፡ ለጨዋታውም ይደርሳል፡፡ በአሁኑ ሰአትም ልምምድ እያደረገ ነው፡፡

 

ጥያቄ – ክለብ አልባው ክሪስቶፈር ማፎምቢ መምረጥዎ ሲያወዛግብ ነበር፡፡ እንዴት ሊመርጡት ቻሉ?

ጥያቄ – ክሪስቶፈር ማፎምቢ መመረጥ አወዛጋቢ እንደሆነ አውቃለሁ፡፡ ነገር ግን እኔ በራሴ መርህ ነው የምመረዋው፡፡ በፈረንሳይ ባለ ፕሮፌሽንል ክለብ ልምምድ እየሰራ ስለሆነ ብዙም የሚያወዛግብ ነገር የለም፡፡

 

ጥያቄ – የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታ ይከታተላሉ?

መልስ – የኢትዮጵያን ብዙ ጨዋታዎች አይቻለሁ፡፡ ከሳኦቶሜ አዲስ አበባ እና ሳኦቶሜ ላይ የተጫወቱትን ፣ ከቡሩንዲ አዲስ አበባ ላይ እንዲሁም ባማኮ ላይ እና አአ ላይ ከማሊ ያደረጉትን ጨዋታም ተመልክቻለሁ፡፡ የ2013 አፍሪካ ዋንጫ ላይ የነበረውን ቡድንም አይቸዋለሁ፡፡ ቡድናችሁ እድለኛ ባይሆንም ጥሩ ጨዋታ ይጫወታል፡፡ የቡድኑን የአጨዋወት ስልት እወደዋለሁ፡፡

 

ጥያቄ – የነገውን ጨዋታ እናሸንፋለን ብላችሁ ታስባላችሁ?

መልስ – የነገውን ጨዋታ እናሸንፋለን፡፡ ባህር ጠለል ከፍ ባለ ከተማ ላይ መጫወታችሁ እንደሚጠቅማችሁ እናውቃለን፡፡ ነገር ግን አሸንፈን እንመለሳለን፡፡

 

ያጋሩ