ኢትዮጵያዊያን ኢንተርናሽናል ዳኞች ከፊፋ የተላከላቸውን ባጅ ተቀብለዋል

ኢትዮጵያውያን ኢንተርናሽናል ዳኞች ዛሬ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የመሰብሰቢያ አዳራሽ ከዓለም አቀፉ እግር ኳስ ማኅበር (ፊፋ) የተላከላቸውን  የ2018/19 የፊፋ ባጅን ተቀብለዋል፡፡

በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የመሰብሰቢያ አዳራሽ ዛሬ በተደረገ ስነ-ስርዓትም በወንዶች ለሰባት ዋና ለሰባት ረዳት እንዲሁም በሴቶች አራት ዋና እና አራት ረዳት ዳኞች በድምሩ ለሀያ ሁለት ኢትዮጵያዊያን ዳኞች ይህ ባጅ ተበርክቶላቸዋል፡፡ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌድሬሽን ስራ አስፈፃሚ አባል እና የዳኞች ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ዮሴፍ ተስፋዬ እና ሌላኛው የስራ አስፈፃሚ አባል አሊሚራህ መሐመድ በክብር እንግድነት በመገኘትም ባጁን ለዳኞች ሰጥተዋል፡፡

ዛሬ የተረከቡት 22 ዳኞች በሙሉ ባለፈው ዓመት ባጅ ያገኙ አዳዲስ እና ነባር ዳኞች ናቸው። በወንዶች ዋና ዳኝነት በዓምላክ ተሰማ፣ በላይ ታደሰ፣ ብሩክ የማነብርሃን፣ ለሚ ንጉሴ፣ ዳዊት አሳምነው፣ አማኑኤል ኃይለሥላሴ እና ቴዎድሮስ ምትኩ ሲሆኑ በረዳት ዳኝነት ደግሞ ትግል ግዛው፣ ክንዴ ሙሴ፣ ሸዋንግዛው ተባበል፣ በላቸው ይታየው፣ ኃይለራጉኤል ወልዳይ፣ ተመስገን ሳሙኤል እና ክንፈ ይልማ ናቸው፡፡

በሴቶች በዋና ዳኝነት ሊዲያ ታፈሰ፣ አስናቀች ገብሬ ጌራወርቅ ከተማ እና ፀሐይነሽ አበበ ሲሆኑ በረዳትነት ወይንሸት አበራ፣ ወጋየሁ ዘውዴ፣ አዜብ አየለ እና ይልፋሸዋ አየለ ናቸው፡፡


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *