በክረምቱ ጅማ አባጅፋርን በሁለት ዓመት ውል የተቀላቀለው ይስሀቅ መኩሪያ ብዙም ሳይቆይ ከክለቡ መሰናበቱ የሚታወስ ሲሆን ተጫዋቹ ለፌዴሬሽኑ ባቀረበው አቤቱታ መሠረት ውሳኔ ተሰጥቷል፡፡
የአማካይ ስፍራ ተጫዋቹ ይስሀቅ መኩሪያ ለክለቡ ከፈረምኩ እና በአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ ላይ ተሰልፌ ከተጫወትኩ በኋላ መሰናበቴ አግባብ አይደለም ሲል ጅማ ደግሞ ከተጫዋቹ ጋር ውል የለኝም በሚል ሲወዛገቡ ቆይተው ፌዴሬሽኑ መረጃዎችን ካጠናከረ በኋላ ውሳኔን ያስተላለፈ ሲሆን በ10 ቀን ውስጥ የተጫዋቹን ጠቅላላ የወር ደመወዙ እንዲከፈለው እና ወደ ክለቡ ተመልሶ እንዲጫወት ውሳኔ ተሰጥቶታል፡፡
ሙሉ የውሳኔ ደብዳቤው ይህን ይመስላል፡-
© ሶከር ኢትዮጵያ
በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡