ቶኪዮ 2020 | ሉሲዎቹ የኦሊምፒክ ማጣርያ ተጋጣሚያቸውን አውቀዋል

በጃፓኗ መዲና ቶኪዮ የሚከናወነው የ2020 ኦሊምፒክ ላይ በሴቶች እግርኳስ ለመሳተፍ የሚደረጉ የማጣርያ ጨዋታዎች በቀጣይ ዓመት መጀመርያ እንደሚከናወኑ ታውቋል።

የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ምክትል ዋና ጸኃፊ አቶ ሰለሞን ገብረሥላሴ ከደቂቃዎች በፊት በተጠናቀቀው የሴቶች ፕሪምየር ሊግ የመጀመርያ የውድድር ዘመን አጋማሽ ስብሰባ ላይ እንደተናገሩት ኢትዮጵያ የመጀመርያ የማጣርያ ጨዋታዋን ከዩጋንዳ ጋር የምታከናውን ሲሆን ከኖቬምበር 4-12 (ህዳር 2012) በሚደረገው የደርሶ መልስ ጨዋታ ኢትዮጰያ የመጀመርያ ጨዋታዋን በሜዳዋ እንደምታደርግ ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ ይህንን ዙር የምታልፍ ከሆነ በቀጣይ ከካሜሩን ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ጋር እንደምትጫወትም ተገልጿል።

የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን በሪዮ 2016 ማጣርያ ላይ ያልተሳተፈ ሲሆን በቀደመው (ለንደን 2012) በኮንጎ ዲ.ሪ 3-0 ድምር ውጤት ተሸንፎ ከመጀመርያው ዙር ተሰናብቷል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *