‘UMBRO’ ከፌዴሬሽኑ ጋር የትጥቅ አቅርቦት ውል መፈራረሙን አስታወቀ

አምብሮ የተሰኘው የእግርኳስ ትጥቆች አምራች ኩባንያ ከኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ጋር የትጥቅ አቅርቦት ውል መፈራረሙን በይፋ አስታወቀ።

የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ያለፉትን ሁለት ዓመታት ከጣልያኑ ኤርያ ጋር ሲሰራ የቆየ ሲሆን ቀሪ ውሉን በማቋረጥ ነው መቀመጫውን በእንግሊዟ ማንቼስተር ያደረገው ግዙፉ የትጥቅ አምራች ኩባንያ አምብሮ ጋር የአራት ዓመታት ውል የተፈራረመው።

አምብሮ ከዚሀ ቀደም የብራዚል እና እንግሊዝ ብሔራዊ ቡድኖች እንዲሁም ማንቼስተር ዩናይትድን ከመሳሰሉ ታላላቅ ቡድኖች ጋር የሰራ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት ኤቨርተን፣ ዌስትሃም፣ ሻልካ፣ ፒኤስቪ እና የመሳሰሉ ክለቦች ጋር እየሰራ ይገኛል።

በፌዴሬሽኑ በኩል ውሉ ይፋ ያልተደረገ ሲሆን የስምምነቱ ዝርዝር እንደደረሰን የምናቀርብ ይሆናል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *