ብሄራዊ ቡድናችን ወደ ኮንጎ ተጉዟል

ትላንት የመጀመርያ ጨዋታውን በሜዳው አድርጎ 3-4 የተሸነፈው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ዛሬ ጠዋት ወደ ኮንጎ ብራዛቪል በርሯል፡፡ የተጋጣሚያችን ልኡካን ቡድንም በተመሳሳይ በመጡበት ቻርተርድ አውሮፕላን ወደ ሃገራቸው ተመልሰዋል::

አሰልጣኝ ዮሃንስ ሳህሌ በፍርድ ቤት ጉዳዮች ምክንያት የትላንቱ ጨዋታ ያመለጠው ራምኬል ሎክን በቡድናቸው ውስጥ ያካተቱ ሲሆን የንግድ ባንኩ አማካይ ቢንያም በላይ ከመጨረሻዎቹ 18 ተጫዋቾች ውጭ ሆኖ በራምኬል ተተክቷል፡፡

ብሄራዊ ቡድናችን 26 የልኡካን ቡድን ይዞ ሲጓዝ አበበ ገላጋይ የቡድን መሪ ሆነው አብረው ተጉዘዋል፡፡

ብሄራዊ ቡድናችን ከ2 ሰአት በኋላ ኮንጎ ብራዛቪል ይደርሳል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ወደ ብራዛቪል የተጓዙት 18 ተጫዋቾች የሚከተሉት ናቸው፡-

ግብ ጠባቂዎች

ታሪክ ጌትነት ፣ አቤል ማሞ

ተከላካዮች

ስዩም ተስፋዬ ፣ ሳላዲን በርጊቾ ፣ አስቻለው ታመነ ፣ ነጂብ ሳኒ ፣ ዋሊድ አታ ፣ ዘካሪያስ ቱጂ

አማካዮች

ጋቶች ፓኖም ፣ አስቻለው ግርማ ፣ በረከት ይሳቅ ፣ በኃይሉ ግርማ ፣ ኤልያስ ማሞ ፣ ሽመልስ በቀለ

አጥቂዎች

ራምኬል ሎክ ፣ ጌታነህ ከበደ ፣ ምንይሉ ወንድሙ ፣ ዳዊት ፍቃዱ

ያጋሩ