የከፍተኛ ሊግ ወቅታዊ መረጃዎች

ምድብ ሀ

ወልዲያ አሰልጣኙን አሰናብቷል

ለአሰልጣኝ አረጋዊ ወንድሙ ባለፈው ወር ማስጠንቀቂያ ሰጥቶ የነበረው ወልዲያ አሁን ደግሞ ማሰናበቱን አስታውቋል። ከምንጮቻቸን ባገኘነው መረጃ መሠረት ወልዲያ ከአሰልጣኙ ጋር ለመለያየት ምክንያት የሆነው ከዳኞች እና አወዳዳሪ አካላት ጋር በተደጋጋሚ ግጭት ውስጥ መግባታቸው እንዲሁም የቡድኑን የአንድነት መንፈስ መገንባት ባለመቻላቸውን እና ከኤሌክትሪክ ጋር በነበረው ጨዋታ ሽንፈት በማስተናገዳቸው እንደሆነ ታውቋል።

አሰልጣኝ አረጋዊ ወንድሙ ስማቸው በሰፊው ከደሴ ቡድን ጋር የተያያዘ ሲሆን በቅርቡ ፊርማቸውን ያኖራል ተብሎ ይጠበቃል።

አክሱም ከተማ

የአክሱም ከተማ ስራ አስኪያጅ አቶ ክንፈ አሰልጣኝ ጌታቸው ዳዊት ከክለቡ ጋር ተለያዩ ተብለው የወጡ መረጃዎች ከእውነታ የራቁ መሆናቸውን ለሶከር ኢትዮጵያ ገልፀዋል።

የመጀመርያ ዙር

የምድብ ሀ የመጀመሪያው ዙር ጨዋታዎች እሁድ የካቲት 17 ተከናውነው የሚጠናቀቅ ይሆናል። መርሐ ግብሩም ይህንን ይመስላል።

ቡራዩ ከተማ 9:00 አውስኮድ
ደሴ ከተማ 9:00 ገላን ከተማ
ለገጣፎ ለገዳዲ 9:00 አቃቂ ቃሊቲ
ወልዲያ 9:00 ሰበታ ከተማ
ወሎ ኮምቦልቻ 9:00 ኢትዮ ኤሌክትሪክ
አክሱም 9:00 ፌዴራል ፖሊስ


ምድብ ለ

ተጠባቂው ጨዋታ

በምድብ ለ መሪው ወልቂጤ ከተማ እና በሶሰት ነጥብ ዝቅ ብሎ የሚገኘው ኢትዮጵያ መድንን የሚያገናኘው ጨዋታ ከወዲሁ ትኩረት ስቧል። ጨዋታው መድን ሜዳ ደጋፊዎችን ከተጫዋቾች የሚለየ አጥር የሌለው በመሆኑ ወደ አዲስ አበባ ስታድየም መለወጡን የእግር ኳስ ፌዴሬሽን ለክለቦቹ በደብዳቤ አሳውቆ የነበረ ቢሆንም አሁን ማምሻውን በተገኘው መረጃ ጨዋታው ወደ መድን ሜዳ መመለሱ ተስምቷል። የአዲስ አበባ እግርኳስ ፌዴሬሽን ከኢትዮጽያ እግርኳስ ፌዴሪሽን ምክትል ፕሪዝዳንት ዐወል አብዱራሂም ጋር ረጅም ውይይት ካደረገ በኋላ ባለሜዳው ኢትዮጵያ መድን በሜዳው የመጫወት መብቱን ሊጠቀም ይገባዋል በሚለው ሀሳብ በመስማማት ወደ መድን ሜዳ መመለሱን ለማወቅ ተችሏል።

የሳምንቱ ጨዋታዎች


እሁድ የካቲት 17 ቀን 2011

ነገሌ አርሲ 9:00 ሀምበሪቾ
ኢትዮጵያ መድን 9:00 ወልቂጤ ከተማ
የካ ክ/ከተማ 9:00 ድሬዳዎ ፖሊስ
አዲስ አበባ ከተማ 9:00 ዲላ ከተማ
ወላይታ ሶዶ 9:00 ናሽናል ሲሚንት
ሀላባ ከተማ 9:00 ኢኮስኮ

ተስተካካይ ጨዋታ

በምድብ ለ ባሳለፍነው ሳምንት ሊደረግ የነበረው የሀምበሪች እና ሀላባ ከተማ ጨዋታ በፀጥታ ጉዳዮች ምክንያት ሳይከናወን መቅረቱ ይታወሳል። ይህ ጨዋታ መቼ እንደሚደረግ የታወቀ ሲሆን የካቲት 24 ቀን 2011 በዱራሜ ይካሄዳል ተብሏል።


ምድብ ሐ

የዲሲፕሊን ኮሚቴ ውሳኔ

የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ዲሲፕሊን ኮሚቴ ጥር 25 ን 2011 በአርባምንጭ ከተማ እና ነቀምት ከተማ መካከል በተካሄደው ጨዋታ ለተከሰተው የስፖርታዊ ጨዋነት ጥሰት አርባምንጭ ላይ የቅጣት ውሳኔ ማስተላለፉን ፌዴሬሽኑ በሳምንቱ መጀመርያ ይፋ አድርጓል። በዚህም መሰረት አርባምንጭ ከተማ አንድ የሜዳውን ጨዋታ በገለልተኛ ሜዳ እንዲያከናውን ሲወሰን 50 ሺህ ብር ቅጣት እንዲከፍልም ተወስኗል።

ከቡድን ቅጣት በተጨማሪ የሁለቱም ቡድኖች አሰልጣኞች የሆኑት መሳይ ተፈሪ እና ቾምቤ ገብረህይወት እያንዳንዳቸው አራት ጨዋታ እና 5ሺህ ብር ቅጣት ሲወሰንባቸው የነቀምት ከተማው ግብ ጠባቂ ኢብሳ አበበ ሶስት ጨዋታ እና 3000 ብር ቅጣት ተላልፎበታል።

የዛሬ ጨዋታዎች ውጤቶች

በርካታ ተስተካካይ ጨዋታዎች ባሉበት ምድብ ሐ ዛሬ ሁለት ጨዋታዎች ተከናውነዋል። በአምስተኛ ሳምንት ተስተካካይ ጨዋታ ቡታጅራ ከተማን የገጠመው ሺንሺቾ 1-0 በማሸነፍ ወደ ሶስተኛ ደረጃ ከፍ ሲል ስልጤ ወራቤ በ2ኛ ሳምንት ተስተካካይ ጨዋታ ቢሾፍቱ አውቶሞቲቭን 1-0 አሸንፏል።

ቀጣይ ጨዋታዎች

የምድብ ሀ እና ለ አንደኛ ዙር በዚህ ሳምንት ፍፃሜያቸውን እንደሚያገኙ ሲጠበቅ የምድብ ሐ ግን ቀሪ ተስተካካይ ጨዋታዎች እየተደረጉ ይቀጥላሉ። በዚህም መሠረት፡-

ረቡዕ የካቲት 20 ቀን 2011

ቢሾፍቱ አወቶ. 09:00 ቤንች ማጂ ቡና
ካፋ ቡና 09:00 ስልጤ ወራቤ
ጅማ አባ ቡና 09:00 ቡታጅራ ከተማ

ማክሰኞ የካቲት 26 ቀን 2011

ቡታጅራ ከተማ 09:00 ቢሾፍቱ አውቶ.
ነቀምት ከተማ 09:00 ካፋ ቡና

የአንደኛ ዙር ፍፃሜ

የምድብ ሐ የመጀመርያ ዙር የመጨረሻ ሳምንት (11ኛ ሳምንት) መጋቢት 1 ቀን 2011 እንደሚካሄድ ታውቋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *