ጅማ አባጅፋር የክለቡ ተጫዋች የሆነው አብዱልፈታህ ከማልን ውል እያለው በማሰናበቱ ምክንያት ፌድሬሽኑ በክለቡ ላይ የእግድ ውሳኔን ማሳለፉን በድረ-ገፁ አስታውቋል፡፡
የፌዴሬሽኑ መረጃ ይህንን ይመስላል :-
በፕሪምየር ሊግ እየተሳተፈ የሚገኘው ጅማ አባጅፋር ተጫዋች የሆነው አብዱልፈታህ ከማል ከመስከረም 2010 ጀምሮ ውሉ በመቋረጡ ተጫዋቹ ባቀረበው አቤቱታ የዲሲፕሊን ኮሚቴ ተመልክቶ ለተጫዋቾቹ ክለቡ ያልከፈለውን ደመወዝ ታስቦ በአምስት ቀናት ውስጥ ክለቡ እንዲከፍለው በ12-06-2010 በፃፈው ደብዳቤ ያሳወቀ ቢሆንም ተግባራዊ ሳይደረግ በመቆየቱ በ12-08-2010 በተፃፈ ሌላ ደብዳቤ ፌዴሬሽኑ ቀጣይ እርማጃ ክለቡ ላይ እንደሚወስድ ያሳወቀ ቢሆንም ይህንን ውሳኔ ተግባራዊ ሳያርግ ቀርቷል፡፡
በመሆኑም ቀሪ የአንድ ዓመት ኮንትራት አምና በክለቡ የነበረው ተጫዋቹ ከፌዴሬስኑ የመጨረሻ የተባለው ውሳኔ ተሰቶታል። በኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን የዲሲፕሊን መመሪያ መሠረት ውሳኔውን ተግባራዊ እስኪያደርግ ከየካቲት 29-2011 ጀምሮ ፌዴሬሽኑ ከሚያዘጋጃቸው ውድድሮች የታገደ መሆኑን ኮሚቴው አሳውቋል፡፡
© ሶከር ኢትዮጵያ
በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡