በጅማ አባጅፋር እና በቀድሞው ተጫዋቹ አብዱልፈታህ ከማል መካከል በተከሰተው አለመግባባት ትናንት የፌዴሬሽኑ የዲሲፕሊን ኮሚቴ ጅማ አባጅፋር የተጫዋቹን ደሞዝ እንዲከፍል እና ይህን እስኪተገብርም የእገዳ ውሳኔ ማስተላለፉ ይታወሳል።
የፌዴሬሽኑን ውሳኔ ተከትሎ የጅማ አባጅፋር የቦርድ አባላት ባደረጉት ድንገተኛ ስብሰባ ውሳኔ እንዳስተላለፉ የክለቡ ፕሬዝዳንት አቶ አጃኢብ አባመጫ ለሶከር ኢትዮጵያ ገልፀዋል። “ከአብዱልፈታህ ጋር በወቅቱ ህጉ በሚያዘው መሰረት በስምምነት ተለያይተን ነበር። ሆኖም ወደኋላ ሄዶ መካሰስ አሁን ባለንበት ደረጃ ጊዜውም ስለራቀ ፌዴሬሽኑ በወሰነው ውሳኔ መሠረት የምንሄድ ይሆናል። የተጫዋቹን የስድስት ወር ደሞዝ በየወሩ ከፋፍለን ለማጠናቀቅም ለፌዴሬሽኑ ጥያቄ አቅርበናል፡፡ ” ሲሉ ፕሬዝዳንቱ የክለቡን ውሳኔ ገልጸዋል።
© ሶከር ኢትዮጵያ
በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡