ምንያህል ተሾመ ለድሬዳዋ ፊርማውን አኑሯል

ያለፉትን ስምንት ወራት ከሜዳ ርቆ የቆየው ምንያህል ተሾመ በሁለተኛው ዙር በርካታ ተጫዋቾችን ለማምጣት እየተንቀሳቀሰ የሚገኘው ድሬዳዋ ከተማን ተቀላቅሏል።

በ1990ዎቹ መጨረሻ በኢትዮጵያ ቡና የእግርኳስ ህይወቱን ከጀመረ በኋላ በ2004 ወደ ደደቢት፤ በ2006 ደግሞ ወደ ቅዱስ ጊዮርጊስ በማምራት ከሦስቱም ጋር የፕሩምየር ሊግ ባለድል የመሆን ታሪክ ያለው አማካዩ በ2010 ፈረሰኞቹን በመልቀቅ ወደ ወልዲያ ካመራ በኋላ ስኬታማ ያልሆነ የውድድር ጊዜን አሳልፏል። ከክለቡ ጋር ከተለያየ በኋላም ያለፉትን ስምንት ወራት ክለብ አልባ ሆኖ ከቆየ በኋላ ዳግም ወደ እግር ኳሱ ተመልሶ ከሁለተኛው ዙር ጀምሮ ለአንድ ዓመት በሚቆይ ውል በምስራቁን ክለብ መቀላቀል ችሏል፡፡

የፈጣሪ አማካይ እጥረት የሚስተዋልበት ድሬዳዋ ከተማ የምንያህል መፈረም ችግሩን በመጠኑ እንደሚቀርፍለት ሲጠበቅ በገበያው ላይ የሚገኙ ተጨማሪ የአማካይ ተጫዋቾችን ለማስፈረም በድርድር ላይ እንደሆነ አሰልጣኝ ስምዖን ዓባይ ለሶከር ኢትዮጵያ ገልፀዋል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *