በከፍተኛ ሊግ ተስተካካይ ጨዋታዎች ነቀምት ደረጃውን ሲያሻሽል ቡታጅራም አሸንፏል


በምድብ ሐ ያለፉትን ሁለት ሳምንታት ሲካሄዱ የቆዩት ተስተካካይ ጨዋታዎች ዛሬ ሲገባደዱ ነቀምት ከተማ እና ቡታጅራ ከተማ አሸንፈዋል።

ነቀምት ላይ ነቀምት ከተማ ከ ካፋ ቡና ትላንት ያደረጉት ጨዋታ በነቀምት 3-1 አሸናፊነት ተጠናቋል። ካፋ ቡናዎች በ32ኛው ደቂቃ በተቆጠረ ጎል ቀዳሚ መሆን ቢችሉም 41ኛው ደቂቃ ላይ ባለሜዳው በዳንኤል ዳዊት ግብ አቻ መሆን ችሏል። በሁለተኛው አጋማሽ በመጨራሻዎቹ ደቂቃዎች ደግሞ ማንያዘዋል ጉዳዬ በጋባቸው ሁለት ተከታታይ ግቦች ነቀምት 3-1 አሸንፏል። ነቀምት በድሉ በመታገዝ ነጥቡን 16 በማድረስ ደረጃውን ወደ 3ኛ ከፍ ማድረግ ችሏል።

ቡታጅራ ላይ ቡታጅራ ከተማ ከቢሾፍቱ አውቶሙቲቭ ያደረጉት ጨዋታ የመጀመርያ አጋማሽ ትላንት ሁለተኛው ደግሞ ዛሬ ተካሂደው ቡታጅራ 3-1 አሸንፏል። ቡታጅራዎች በ27ኛው ደቂቃ ተስፋዬ አመርጋ እና በ43ኛው ደቂቃ ክንዴ አቡቹ ጎሎች 2-1 እየመሩ ወደ እረፍት ያመሩ ሲሆን በእለቱ በጣለው ዝናብ ምክንያት መቀጠል ባለመቻሉ ዛሬ 5:00 ላይ ሁለተኛውን አጋማሽ ማድረግ ችለዋል። በ70ኛው ደቂቃ ተስፋዬ አመርጋ ተጨማሪ ግብ ለቡታጅራ አስቆጥሮም ጨዋታው 3-1 መጠናቀቅ ችሏል።

በርካታ ተስተካካይ ጨዋታዎች የነበሩበት የምድብ ሐ በአሁኑ ወቅት ሙሉ ለሙሉ ሲጠናቀቁ የአንደኛው ዙር የመጨረሻ ሳምንት (11ኛ ሳምንት) በመጪው እሁድ የሚከናወን ይሆናል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *