በክረምቱ የዝውውር ወቅት አዳማ ከተማን ተቀላቅሎ የነበረው አማካዩ ሐብታሙ ሸዋለም ከአዳማ ከተማ ጋር በስምምነት ተለያይቷል፡፡
በክረምቱ ወልዲያን ለቆ ወደ አዳማ ከተማ ያመራውና በክለቡ ቀሪ የስድስት ወራት የነበረው ሐብታሙ በዘንድሮው የውድድር ዓመት በአንድም ጨዋታ ላይ የመጀመርያ ተሰላፊ ሆኖ ያልተጫወተ ሲሆን በ9 ጨዋታዎች በተጠባባቂነት ቢጀምርም በሁለት አጋጣሚዎች ብቻ ከተጠባባቂ ወንበር በመነሳት በድምሩ 58 ደቂቃዎችን ተጫውቷል። ከሳምንት በፊት ክለቡን የተቀላቀለው ብሩክ ቃልቦሬን መምጣት ተከትሎም ይበልጥ የመሰለፍ እድል የማግኘቱ ጉዳይ አጠራጥሮ ነበር። በዚህም ኮንትራቱን በስምምነት በማቋረጥ ከአዳማ ጋር መለያዩቱ ተገልጿል። ወደ ሌላ የፕሪምየር ሊግ ቡድን ለማምራት ከጫፍ መድረሱም ታውቋል።
አማካዩን ጨምሮ በአጠቃላይ አራት ተጫዋቾችን የለቀቀው አዳማ ከተማ ሁለት ተጫዋቾችን በምትኩ አስፈርሟል።
© ሶከር ኢትዮጵያ
በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡