ሀዋሳ ከተማ ጋናዊ አጥቂ አስፈርሟል

ሀዋሳ ከተማ ጋናዊው አጥቂ ክዋሜ አትራምን በድጋሚ ወደ ኢትዮጵያ በመመለስ ወደ ክለቡ ቀላቅሎታል፡፡

በአጥቂ ስፍራ ላይ ከፍተኛ ክፍተት የሚታይበት ሀዋሳ ከተማ ጋናዊ አጥቂ አትራም ኩዋሜን በአንድ ዓመት ውል አስፈርሟል፡፡ በ2010 ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት ድሬዳዋ ከተማ መጫወት የቻለው የ29 አመቱን አትራም በጋናው ትልቅ ክለብ አሻንቲ ኮቶኮ የእግር ኳስ ህይወቱን የጀመረ ሲሆን ከ2006-2009 ደግሞ በግብፁ ዋዲ ዳግላ፣ በታይላንዱ ቲኦቲ፣ በቬትናሙ ሀኖይ ቲ ኤንድ ቲ፣ በደቡብ አፍሪካዎቹ ስዋሎውስ እና ሚላኖ ዩናይትድ በዲ.ሪ ኮንጎ ስፖርቲቭ ባዛኖ ተጫውቶ አሳልፏል፡፡ አምና ወደ ድሬዳዋ ካማምራቱ በፊትም በዛምቢያው ዛናኮ መጫወት ችሏል፡፡

ከሁለት ተጫዋቾች ጋር የተለያየው ሀዋሳ ከተማ ከፍተኛ ክፍተት በሚታይበት የፊት መስመር ቦታ ላይ እስራኤል እሸቱንና ገብረመስቀል ዱባለን ያካተተ ሲሆን አሁን ደግሞ የጋናዊው አጥቂን መምጣት ተከትሎ አማራጩን እንደሚያሰፋለት ይጠበቃል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *