ባህር ዳር ከተማ እና ፋሲል ከነማ የወዳጅነት ጨዋታ አዘጋጁ

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ እረፍት ላይ መሆኑን ተከትሎ ሁለተ የሊጉ ተሳታፊዎች ፋሲል ከነማ እና ባህር ዳር ከተማ በአማራ ክልል በተለያየ ምክንያት ለተፈናቀሉ ወገኖች የሚውል የወዳጅነት ጨዋታ አዘጋጅተዋል።

በሁለቱ ክለቦች በጣምራ የተዘጋጀው ይህ ጨዋታ ማክሰኞ መጋቢት 4 በባህርዳር ኢንተርናሽናል ስታዲየም 09:00 ላይ ይደረጋል። ጨዋታው የተዘጋጀበት ዋና ዓላማ በተለያየ ምክንያት የተፈናቀሉት ወገኖች ለመርዳት ቢሆንም ከዋናው ዓላማ ጎን ለጎን ስፖርቱ ለሠላም መቆሙን ማሳያ እንዲሁም ሁለቱ ቡድኖች ከጨዋታ እንዳይርቁ የወዳጅነት ጨዋታ ማድረጉ የሚሠጠውን ጠቀሜታ ግምት ውስጥ ያስገባ ነው።

ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በማህበራዊ ጉዳዮች የሚበረታታ እንቅስቃሴ እያደረጉ የሚገኙት የኢትዮጵያ ክለቦች ከዚህ ቀደም የአማራ ክልል ክለቦች እና ቅዱስ ጊዮርጊስ በጣና ሃይቅ የበቀለው እምቦጭ አረም ዙርያ ግንዛቤ ለመፍጠር ውድድር አዘጋጅተው እንደነበር ሲታወስ በትግራይ ኢንተርናሽናል ስታድየም ተመሳሳይ አላማ የነበረው ለተፈናቀሉ ወገኖች ማሳሰቢያ መቐለ ከ ወልዋሎ እንዲሁም ኢትዮጵያ ቡና ከ ኢትዮ ኤሌክትሪክ በቅርቡ በህይወት ላጣናቸው ሥዩም አባተ ህክምና የሚውል ጨዋታ መከናወኑ ይታወሳል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *