አሰልጣኝ ዘማርያም ወልደጊዮርጊስ ቅጣታቸውን ቢያጠናቅቁም በልምምድ ላይ አልተገኙም

በ2010 የውድድር ዘመን ወልዲያ ከፋሲል ከነማ ባደረጉት የሊግ ጨዋታ ለተፈጠረው ሁከት መነሻ ናችሁ በማለት የዲሲፕሊን ኮሚቴ ለአንድ ዓመት ቅጣት ጥሎባቸው የቆዩት አሰልጣኝ ዘማርያም ወልደጊዮርጊስ ቅጣታቸውን ቢያጠናቀቁም ጅማ አባጅፋር የስድስት ቀናት መደበኛ ልምምድ ላይ አልተገኙም።

አሰልጣኝ ዘማርያም ወልደጊዮርጊስ ያለፉትን ስድስት ወራት ምንም እንኳ ቡድኑን በቴክኒካል ቦታ ላይ ተቀምጠው መምራት ባይችሉም የቡድኑ ዋና አሰልጣኝ በመሆን ጅማ አባ ጅፋርን አገልግለዋል። የፊታችን እሁድ ጅማ አባ ጅፋር ከአዳማ ከተማ በሚያደርገው የሁለተኛው ዙር የውድድር አጋማሽ የመጀመርያ ጨዋታ ላይ ቡድኑ በተሟላ ሁኔታ በሚያደርገው መደበኛ ልምምድ ላይ ግን አሰልጣኝ ዘማርያም ወልደጊዮርጊስ ተገኝተው ልምምድ እያሰሩ አይደለም። ምክንያቱ ምን እንደሆነ ወደ አሰልጣኙ ያለፉትን ቀናት በስልክ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት ስልካቸው ዝግ በመሆኑ ሀሳባቸውን ማካተት ያልቻልን ሲሆን በጅማ አባጅፋር በኩል በልምምድ ላይ ቡድኑን እያሰለጠኑ አለመሆኑን አረጋግጠው ምክንያቱ ምን እንደ ሆነ ዝርዝር መረጃዎቹን ከመግለፅ ግን ተቆጥበዋል።

ጅማ አባጅፋር እሁድ በሚያደርገው የሁለተኛው ዙር አጋማሽ የመጀመርያ ጨዋታ ያለ ዋና አሰልጣኙ ወደ ሜዳ ይገባል ወይስ ዛሬ አልያም ነገ ቡድኑን ተቀላቅለው በዋና አሰልጣኙ ይመራል የሚለው በቀጣዮቹ ጥቂት ቀናት የምናየው ይሆናል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *