አብርሀም መብራቱ የኦሊምፒክ ቡድኑን ስብስብ ወደ ሀያ ስድስት ቀንሰዋል

የኢትዮጵያ ከ23 ዓመት በታች ኦሊምፒክ ብሔራዊ ቡድን ከማሊ ጋር በያዝነው ወር ላለበት የማጣሪያ ጨዋታ ለ34 ተጫዋቾች ጥሪን በማድረግ ከየካቲት ወር መጨረሻ ጀምሮ በአዲስ አበባ ስታዲየም ዝግጅቱን ሲያደርጉ ቆይተዋል።

ከቀናት በፊት የሲሼልስ ብሔራዊ ቡድንን በወዳጅነት ጨዋታ ገጥመው በአቡበከር ነስሩ ብቸኛ ግብ ካሸነፉ በኋላ አሰልጣኙ በጨዋታው እና በልምምድ በተመለከቱት መሠረት የቡድኑን ስብስብ ከ34 ወደ 26 ዝቅ ማድረጋቸው ታውቋል። ዜናው ፈረደ (ባህርዳር)፣ ይበልጣል ሺባባው (ኢኮስኮ)፣ እንየው ካሳሁን (ወልዋሎ)፣ አብዱልከሪም ወርቁ (ወልቂጤ)፣ ሰለሞን ወዴሳ (መድን)፣ ያሬድ ከበደ (መቐለ)፣ ስንታየሁ መንግስቱ (አርባምንጭ)፣ አሚር አህመድ (ሞውሼል/ ኤኤፍሲ) ከስብስቡ ውጪ የሆኑ ተጫዋቾች ናቸው፡፡

የ26 ተጫዋቾች ዝርዝር

ግብ ጠባቂዎች

ምንተስኖት አሎ (ባህርዳር)፣ ተክለማርያም ሻንቆ (ሀዋሳ)፣ ጆርጅ ደስታ (መድን)

ተከላካዮች
ወንድሜነህ ደረጀ (ባህርዳር ከተማ)፣ ፈቱዲን ጀማል (ሲዳማ ቡና)፣ ሸዊት ዮሐንስ (ስሑል ሽረ)፣ አብርሀም ሁሴን (ኤሌክትሪክ)፣ ጌቱ ኃይለማርያም (ሰበታ)፣ ሳሙኤል ተስፋዬ (ቅዱስ ጊዮርጊስ)፣ ደስታ ደሙ (ወልዋሎ)፣ ደስታ ዮሐንስ (ሀዋሳ)፣ ዳዊት ወርቁ (ደደቢት)

አማካዮች

ሱራፌል ዳኛቸው (ፋሲል)፣ ሐብታሙ ተከስተ (ፋሲል)፣ ቴዎድሮስ ታፈሰ (መከላከያ)፣ ከነዓን ማርክነህ (አዳማ)፣ አማኑኤል ዮሐንስ (ኢትዮጵያ ቡና)፣ የዓብስራ ተስፋዬ (ደደቢት)፣ አፈወርቅ ኃይሉ (ወልዋሎ)

አጥቂዎች

እዮብ ዓለማየሁ (ወላይታ ድቻ)፣ አማኑኤል ገብረሚካኤል (መቐለ)፣ ፍቃዱ አለሙ (መከላከያ)፣ አቡበከር ናስር (ኢትዮጵያ ቡና)፣ ሐብታሙ ገዛኸኝ (ሲዳማ ቡና)፣ እስራኤል እሸቱ (ሀዋሳ)፣ በረከት ደስታ (አዳማ)


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *