በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ደደቢት እና መከላከያ የውድድር ዘመናቸውን በድል ከፍተዋል

ትላንት የተጀመረው የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ የሰሜን/መካከለኛው ዞን ውድድር ዛሬ ቀጥሎ ውሏል፡፡ መከላከያ እና ደደቢትም የውድድር ዘመናቸውን በድል ከፍተዋል፡፡

በ9፡00 ቅድተ ማርያምን የገጠመው መከላከያ 4-2 አሸንፏል፡፡ መከላከያ ምስር ኢብራሂም በ3ኛው ደቂቃ በስቆጠረችው ግብ ሲመራ በ10ኛው ደቂቃ መዲና አወል መከላከያን ግብ ጠባቂ በማለፍ ቅድሰ ማርያምን አቻ ያደረገች ግብ ከመረብ አሳርፋለች፡፡ አክበረት ገብረፃዲቅ በ22ኛው ደቂቃ መከላከያን በድጋሚ መሪ አድርጋ የመጀመርያው አጋማሽ በመከላከያ 2-1 መሪነት ተጠናቋል፡፡

በ2ኛው አጋማሽ የመጀመርያዎቹ ደቃቂዎች የተሰጠውን የፍፁም ቅጣት ምት መዲና አወል ወደ ግብነት ቀይራ ቅድስተ ማርያምን አቻ ብታደርግም በ53ኛው ደቂቃ ፍቅርተ ብርሃኑ ግብ አስቆጥራ በድጋሚ መከላከያዎች መምራት ችለዋል፡፡ በ90ኛው ደቂቃ ደግሞ የምስራች ላቀው የመከላከያን 4ኛ ግብ ከመረብ አሳርፋለች፡፡

የሊጉ ታላላቅ ቡድኖችን ያገናኘው የእለቱ 2ኛ ጨዋታ በደደቢት 2-1 አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡ ደደቢትም ከ2 ሳምንት በፊት በአሸናፊዎች አሸናፊ ዋንጫ የደረሰበትን ሽንፈት ተበቅሏል፡፡

ደደቢት በ25ኛው ደቂቃ ሎዛ አበራ ባስቆጠረችው የፍፁም ቅጣት ምት ሲመራ የ2007 የሊጉ ከፍተኛ ግብ አግቢ ሎዛ በ33ኛው ደቂቃ በድጋሚ ግብ አስቆጥራ የደደቢት መሪነት አጠናክራለች፡፡

ጨዋታው በደደቢት 2-0 መሪነት እስከ ጨዋታው መገባደጃ ደቂቃዎች የዘለቀ ሲሆን በ90ኛው ደቂቃ ብሩክታዊት ግርማ የንግድ ባንክን አንድ ግብ ከመረብ አሳርፋ ጨዋታው በደደቢት 2-1 አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡

የ1ኛ ሳምንት ውጤቶች

ቅዱስ ጊዮርጊስ 9-1 እቴጌ

ልደታ 1-3 ኢትዮጵያ ቡና

ደደቢት 2-1 ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

ቅድስተ ማርያም 2-4 መከላከያ

 

ከፍተኛ ግብ አግቢዎች

4- ትመር ጠንክር (ቅዱስ ጊዮርጊስ)

3- ሄለን ሰይፉ (ቅዱስ ጊዮርጊስ)

2- መዓድን ሳህሉ (ኢትዮጵያ ቡና)

2- ሎዛ አበራ (ደደቢት)

2- መዲና አወል (ቅድስተ ማርያም)

 

ያጋሩ