ለኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን የኦሊምፒክ ማጣርያ ዝግጅት 30 ተጫዋቾች ተጠርተዋል

በኢትዮጵያ አቆጣጠር በ2012 ክረምት ላይ ለሚካሄደው የቶኪዮ ኦሊምፒክ በሴቶች እግርኳስ የማጣርያ ውድድር ላይ የሚሳተፈው የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን የመጀመርያ የማጣርያ ጨዋታውን መጋቢት 25 ከዩጋንዳ ጋር በአዲስ አበባ ስታድየም የሚያከናውን ሲሆን ለዚህም ዝግጅት እንዲረዳ አሰልጣኝ ሠላም ዘርዓይ ለ30 ተጫዋቾች የመጀመርያ ጥሪ አድርጋለች። 

አሰልጣኟ ለሶከር ኢትዮጵያ እንደገለፀችሁ ከሆነ ከፊታችን ሀሙስ ጀምሮ ወደ ልምምድ መርሀ ግብር በመግባት ባለው የጊዜ መጣበብ ምክንያትም ሰኞ ዕለት የመጨረሻ 25 ተጫዋቾች ይፋ ይደረጋሉ። የብሔራዊ ቡድኑ ዋና አሰልጣኝ ሆና ባሳለፍነው ሳምንት የተሾመችው ሠላም ዘርዓይ በምክትል አሰልጣኝነት የልደታ ክፍለ ከተማው ብዙዓየሁ ዋዳ፣ በግብ ጠባቂ አሰልጣኝነት ደግሞ  የኢትዮጵያ ቡናው ፀጋዘዓብ አስገዶምን ምርጫዋ እንዳደረገች ገልፃ በዚህ አጭር ጊዜ የተቻለውን ሁሉ በማድረግ የመጀመሪያ የማጣሪያ ጨዋታን በድል ለመወጣት ጥረት እንደምታደርግ ተናግራለች።

ከተጠሩት 30 ተጫዋቾች መካከል 29 ተጫዋቾች ከአንደኛ ዲቪዝዮን ሲጠሩ የመቐለ 70 እንደርታዋ ዮርዳኖስ ምዑዝ ብቸኛዋ ከሁለተኛ ዲቪዝዮን የተመረጠች ተጫዋች ሆናለች።

የቀድሞው የፌስቡክ ገፃችን በኛ ቁጥጥር ስር የማይገኝ በመሆኑ አዲሱ ገፃችንን ሊንኩን በመከተል ላይ ያድርጉ – facebook.com/SoccerEthiopia

ዝርዝሩ ይህንን ይመስላል:-

ግብ ጠባቂዎች

ማርታ በቀለ (መከላከያ)፣ ታሪኳ በርገና (ጥረት ኮርፖሬት)፣ አባይነሽ ኤርቄሉ (ሀዋሳ ከተማ)፣ ምህረት ተሰማ (ጌዴኦ ዲላ)

ተከላካዮች

መስከረም ካንኮ (አዳማ ከተማ)፣ መሠሉ አበራ (መከላከያ)፣ ገነሜ ወርቁ (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)፣ አሳቤ ሙሶ (ጥረት ኮርፖሬት)፣ ታሪኳ ደቢሶ (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)፣ ብዙዓየሁ ታደሠ (ኢትዮ ንግድ ባንክ)፣ እፀገነት ብዙነህ (አዳማ ከተማ)፣ ትዕግስት ኃይሌ (ቅዱስ ጊዮርጊስ)፣ ናርዶስ ዘውዴ (አዳማ ከተማ)፣ ነፃነት ፀጋዬ (አዳማ ከተማ)

አማካዮች

ሕይወት ዳንጊሶ (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)፣ እመቤት አዲሱ (መከላከያ)፣ ብርሃን ኃይለሥላሴ (ቅዱስ ጊዮርጊስ)፣ ሰናይት ቦጋለ (አዳማ ከተማ)፣ ብርቱካን ገብረክርስቶስ (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)፣ ትዕግስት ያደታ (ኢትዮ ንግድ ባንክ)፣ ዓለምነሽ ገረመው (ኢትዮ ኤሌክትሪክ)፣ አረጋሽ ከልሳ (መከላከያ)፣ ዮርዳኖስ ምዑዝ (መቐለ 70 እንደርታ)

አጥቂዎች

ረሃማ ዘርጋው (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)፣ ሎዛ አበራ (አዳማ ከተማ)፣ ሴናፍ ዋኩማ (አዳማ ከተማ)፣ ሰርካዲስ ጉታ (አዳማ ከተማ)፣ ምርቃት ፈለቀ (ሀዋሳ ከተማ)፣ ሔለን እሸቱ (መከላከያ)፣ ምስር ኢብራሂም (ጥረት ኮርፖሬት)

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *