የማሊ ከ23 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ከጊዜ ጋር ግብግብ ገጥሟል

የኢትዮጵያን ብሔራዊ ቡድንን የሚገጥመው የማሊ ከ23ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን የወዳጅነት ጨዋታ ሰርዞ ወደ ኢትዮጵያ ተጓዘ፡፡

ከኢትዮጵያ ጋር የሚደረገውን የማጣሪያ ጨዋታ ቅዳሜ መጋቢት 14 እንደሆነ በማሰብ ሀሙስ መጋቢት 12 ወደ አዲስ አበባ ለመጓዝ ቀጠሮ ይዞ የነበረው የማሊ ብሔራዊ ቡድን ትላንት መጋቢት 10 ቀን ከኤ.ኤስ ሬያል ድ ባማኮ ጋር ሊያደርግ የነበረውን የወዳጅነት ጨዋታ ሰርዞ ወደ ኢትዮጵያ ለመጓዝ ተገዷል፡፡

የቀድሞው የፌስቡክ ገፃችን በኛ ቁጥጥር ስር የማይገኝ በመሆኑ አዲሱ ገፃችንን ሊንኩን በመከተል ላይ ያድርጉ – facebook.com/SoccerEthiopia

የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) ቀደም ብሎ መጋቢት 14 ቀን ሊደረግ የነበረውን ጨዋታ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንን ጥያቄ ተከትሎ ወደ መጋቢት 12 መቀየሩንና ለሁለቱም ቡድኖች ማስታወቁን መዘገባችን ይታወሳል፡፡ ነገር ግን የጨዋታውን ቀን መቀየር ልብ ያላሉት የማሊ ብሔራዊ ቡድን ባለስልጣናት ከጊዜ ጋር ግብግብ ገጥመዋል፡፡ ከውጭ ሃገር መጥተው ቡድኑን የሚቀላቀሉትን ተጫዋቾች በሜዳ ላይ ለመሞከር በማሰብ በትናንትናው ቀን ከኤ.ኤስ ሬያል ድ ባማኮ ክለብ ጋር የወዳጅነት ጨዋታ ለማድረግ ቀጠሮ የተያዘ ቢሆንም ጨዋታው ሀሙስ መጋቢት 12 መሆኑን ለቴክኒክ ኮሚቴው ትናንት በደረሰው መረጃ መሰረት የወዳጅነት ጨዋታውን ሰርዘው ለአዲስ አበባ ጉዞ እንዲዘጋጁ ለአሰልጣኙ ፋኒዬሪ ዲያራ ተነግሯቸዋል፡፡

በዚህ የተደናገጡት አሰልጣኙ ከአውሮፓ የመጡትን ተጫዋቾችን ትተው ወደ ኢትዮጵያ ሊመጡ እንደሚችሉ አላሳን ሲሱማ የተባለው የማሊፉት የእግር ኳስ ድረ-ገጽ ጋዜጠኛ ዘግቧል፡፡
የማሊ ከ23 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ዛሬ አዲስ አበባ እንደሚገባ ሲጠበቅ ነገ (ሐሙስ) መጋቢት 12 በአስር ሰዓት የኢትዮጵያ አቻውን ይገጥማል፡፡


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *