መቐለ 70 እንደርታ ሄኖክ ኢሳይያስን ወደ ቡድኑ ቀላቅሏል

ሊጉን በሰፊ ልዩነት እየመሩ የሚገኙት እና በዝውውሩ በሰፊው ይሳተፋሉ ተብለው ሲጠበቁ የነበሩት ምዓም አናብስት በዚህ የዝውውር መስኮት ሁለተኛ ፈራሚያቸው የሆነው የአማካይ ክፍል ተጫዋቹ ሄኖክ ኢሳይያስን ለማስፈረም ከስምምነት ደርሰዋል።

ባለፈው የውድድር ዓመት ከጅማ አባጅፋር ጋር የፕሪምየር ሊጉን ዋንጫ አንስቶ ወደ ወላይታ ድቻ በማምራት ላለፉት ስድስት ወራት ከክለቡ ጋር ቆይታ ያደረገው የቀድሞ የስሑል ሽረ ፣ ደደቢት እና የጅማ አባጅፋር አማካይ ከዮናስ ገረመው እና አሚን ነስሩ ቀጥሎ የቀድሞ አሰልጣኙን ፈለግ በመከተል ወደ መቐለ ያመራ ሶስተኛ ተጫዋች መሆን ችሏል።

የቀድሞው የፌስቡክ ገፃችን በኛ ቁጥጥር ስር የማይገኝ በመሆኑ አዲሱ ገፃችንን ሊንኩን በመከተል ላይ ያድርጉ – facebook.com/SoccerEthiopia

ባለፈው ሳምንት ጋናዊው ተከላካይ ክዌኩ አንዶህን ያስፈረሙት መቐለዎች በሁለተኛው ዙር ጠንክረው ለመቅረብ በቀጣይ የዝውውር ቀናት ተጨማሪ ተጫዋቾች ያስፈርማሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ከወላይታ ድቻ ቀሪ የአንድ ዓመት ከስድስት ወር እያለው ከክለቡ በስምምነት የተለያየው ተጫዋቹ ያለፉትን ሁለት ቀናት ከመቐለ 70 እንደርታ ጋር ልምምድ የሰራ ሲሆን ዛሬ ከሰዓት በይፋ ለክለቡ ፊርማውን እንደሚያኖር ለማወቅ ተችሏል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *