ሀምበሪቾ ዱራሜ ዓለማየሁ ዓባይነህን በዋና አሰልጣኝነት ሾሟል

የቀድሞው አርባምንጭ ከተማ እና ሲዳማ ቡና አሰልጣኝ ዓለማየሁ ዓባይነህ የከፍተኛ ሊጉ ክለብ ሀምበሪቾ ዱራሜ አሰልጣኝ ሆነው ተሹመዋል።
በከፍተኛ ሊግ ምድብ ለ የሚገኘውና በ4ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጦ የመጀመርያውን ዙር ያጠናቀቀው ሀምበሪቾ ዱራሜ ከትላንት በስቲያ ዋና አሰልጣኙ ያሬድ አበጀን ካሰናበተ በኋላ ዛሬ ዓለማየሁ ዓባይነህን ቀጥሯል።

የቀድሞው የፌስቡክ ገፃችን በኛ ቁጥጥር ስር የማይገኝ በመሆኑ አዲሱ ገፃችንን ሊንኩን በመከተል ላይ ያድርጉ – facebook.com/SoccerEthiopia

ከሲዳማ ቡና ጋር ከተለያዩ በኋላ ያለ ክለብ ለ10 ወራት የቆዩት የቀድሞው የአርባምንጭ ጨርቃጨርቅ ተጫዋች እና የአርባምንጭ ከተማ አሰልጣኝ ዓለማየሁ የምድቡን ፉክክር በበላይነት በመወጣት ሀምበሪቾን ወደ ፕሪምየር ሊጉ የማሳደግ ፈተና ይጠብቃቸዋል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *