ኢትዮጵያዊያን ዳኞች የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያን እንዲመሩ ተመርጠዋል

የፊታችን ዕሁድ ቤኒን ላይ ቤኒን ከቶጎ በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የሚያደርጉትን ወሳኝ ጨዋታ ኢትዮጵያዊያን ዳኞች ይመሩታል።

በምድብ መ አስቀድማ ወደ አፍሪካ ዋንጫው ማለፏን ካረጋገጠችው አልጄርያ እና መውደቋ ከተረጋገጠው ጋምቢያ ጋር የተደለደሉት ቤኒን እና ቶጎ በቅደም ተከተል 7 እና 5 ነጥቦች ይዘው በቤኒኗ መዲና ኮቶኑ በሚገኘው ስታደ አሚቴ ጨዋታቸውን የሚያደርጉ ሲሆን በሚያስመዘግቡት ውጤትም ወደ ግብፅ የሚወስዳቸውን ትኬት የመቁረጥ እጣ ፈንታቸውን ይወስናሉ።

የቀድሞው የፌስቡክ ገፃችን በኛ ቁጥጥር ስር የማይገኝ በመሆኑ አዲሱ ገፃችንን ሊንኩን በመከተል ላይ ያድርጉ – facebook.com/SoccerEthiopia

ባሳለፍነው ሳምንት ጊኒ ላይ የጊኒው ክለብ ሆሮያ ከኦሮርላንዶ ፓይሬትስ ያደረጉትን የአፍሪካ ቻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታ በዓምላክ ተሰማ ከረዳቶቹ ትግል ግዛው እና ተመስገን ሳሙኤል እንዲሁም በአራተኛ ዳኝነት ደግሞ በላይ ታደሰ ጋር በመሆን መርተው የተመለሱ ሲሆን አሁን ደግሞ የአንድ ዳኛ ለውጥ ብቻ ተደርጎ ሶስቱ በድጋሚ ይህን የአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ ጨዋታ ይመራሉ። በመሀል ዳኝነት ባምላክ ተሰማ፣ በረዳት ዳኝነት ትግል ግዛው እና ተመስገን ሳሙኤል፣ በአራተኛ ዳኝነት ደግሞ ቴዎድሮስ ምትኩ እንዲመሩም በካፍ ተመድበዋል፡፡


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *