ቅድመ ጨዋታ ዳሰሳ | ሀዋሳ ከተማ ከ ፋሲል ከነማ

የዛሬ ቅድመ ዳሰሳችን የመጨረሻ ትኩረት የሀዋሳ እና የፋሲል ጨዋታ ነው።

አምስት እና አራተኛ ደረጃ ላይ የሚገኙት ሀዋሳ ከተማ እና ፋሲል ከነማ ነገ 09፡00 ላይ በሀዋሳው ሰው ሰራሽ ስታድየም ይገናኛሉ። በወልዋሎ የ1-0 ሽንፈት የገጠማቸው ሀዋሳዎች በዋንጫ ፉክክሩ ውስጥ ከነበራቸው ቦታ እየተንሸራተቱ ከመሪው ጋር የነበራቸው ልዩነት ወደ 14 ከፍ ብሏል። ዓመቱን በጅመሩበት አኳኋን መቀጠል ባለመቻላቸውም ከነገው ጨዋታ ሙሉ ነጥብ ቢያሳኩ እንኳን ማሻሻል የሚችሉት አንድ ደረጃ ብቻ ነው። ሀዋሳዎች ደስታ ዮሃንስ ፣ ተክለማርያም ሻንቆ እና እስራኤል እሸቱን ኦሊምፒክ ቡድን ጥሪ ምክንያት ገብረመስቀል ዱባለን ደግሞ በጉዳት በነገው ጨዋታ የማይጠቀሙ ሲሆን አዲስዓለም ተስፋዬ በሁለተኛ ቢጫ ካርድ ቅጣት ከቡድኑ ውጪ ሲሆን ብሩክ በየነ ከጉዳት የሚመለስ ይሆናል፡፡ የቀድሞው ክለባቸውን የሚገጥሙት አሰልጣኝ ውበቱ አባተም በኦሊምፒክ ቡድን ምርጫ ምክንያት ሁለቱ አማካዮቻቸው ሱራፌል ዳኛቸው እና ሀብታሙ ተከሰተን ግልጋሎት የማያገኙ ሲሆን ጀማል ጣሰው እና አብዱራህማን ሙባረክ ደግሞ በጉዳት ሳቢያ ወደ ሀዋሳ አልተጓዙም። ለሙጂብ ቃሲም የአጥቂነት ሚና መስጠት የጀመሩት ፋሲሎች የነጥብ ስብስባቸውን ከ30 በላይ ወዳደረሱ ክለቦች ዝርዝር ውስጥ ለመቀላቀል የሚፋለሙ ይሆናል።

የእርስ በርስ ግንኙነቶች እና እውነታዎች

– ሁለቱ ቡድኖች በሊጉ ከተኙባቸው አምስት ጨዋታዎች ስምንት ግቦች ያስቆጠረው ሀዋሳ ከተማ ሁለት ጊዜ ሲያሸንፍ ፋሲል ደግሞ ዘንድሮ በመጀመሪያው ዙር 3-1 ያሸነፈበትን ድል አስመዝግቦ የግብ መጠኑን ስድስት አድርሷል ፤ ቀሪዎቹ ሁለት ጨዋታዎች በአቻ ውጤት እየተጠናቀቁ ነው።

– ሀዋሳ ላይ ዘጠኝ ጨዋታዎችን ያደረጉት ሀዋሳ ከተማዎች በምንም ጨዋታ ነጥብ ያልተጋሩ ሲሆን ስድስቱን አሸንፈው በሦስቱ አቻ ተለያይቷል።

– ከሜዳቸው ስምንት ጊዜ የወጡት ፋሲል ከነማዎች አራት ጊዜ ነጥብ ሲጋሩ ሁለት ጊዜ ደግሞ ድል አድርገው በሌሎች ሁለት ጨዋታዎች ተሸንፈዋል።

ዳኛ

– ጨዋታውን በመሀል ዳኝነት የሚመራው ኢንተርናሽናል ዳዊት አሰምነው እስካሁን በስምንት ጨዋታዎች አንድ የቀይ ካርድ እና አንድ የፍፁም ቅጣት ምት ሲሰጥ 18 የቢጫ ካርዶችን መዟል።

ግምታዊ አሰላለፍ

ሀዋሳ ከተማ (3-5-2)

ሶሆሆ ሜንሳህ

ወንድማገኝ ማዕረግ – መሣይ ጳውሎስ – ላውረንስ ላርቴ

ዳንኤል ደርቤ –ፍቅረየሱስ ተወልደብርሀን – ሄኖክ ድልቢ– ታፈሰ ሰለሞን – አክሊሉ ተፈራ

አዳነ ግርማ – ቸርነት አዉሽ

ፋሲል ከነማ (4-3-3)

ሚኬል ሳማኬ

ሰዒድ ሁሴን – ከድር ኩሊባሊ – ያሬድ ባየህ – አምሳሉ ጥላሁን

ሠለሞን ሐብቴ – ኤፍሬም ዓለሙ – በዛብህ መለዮ

ዓለምብርሀን ይግዛው – ሙጂብ ቃሲም – ሽመክት ጉግሳ


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *