ኢትዮጵያ ከቶኪዮ ኦሊምፒክ ማጣርያ ውጪ ሆናለች

በ2020 የቶኪዮ ኦሊምፒክ ማጣርያ አካል በሆነውና በግብፅ አስተናጋጅነት ለሚካሄደው የአፍሪካ ከ23 ዓመት በታች ዋንጫ ማጣርያ ላይ ተሳታፊ የነበረው የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ቡድን በአንደኛው ዙር ማጣርያ የመልስ ጨዋታ በማሊ 5-1 ድምር ውጤት ተሸንፎ ከማጣርያው ውጪ ሆኗል።

ባሳለፍነው ሐሙስ አዲስ አበባ ስታድየም ላይ 1-1 ተለያይቶ ወደ ባማኮ ያመራው ብሔራዊ ቡድኑ ዛሬ ምሽት ባደረገው ጨዋታ 4-0 ተሸንፏል። በ39ኛው ደቂቃ ወንድሜነህ ደረጀ በጎውኔ ዲያንጋዱ ላይ በሰራው ጥፋት የተገኘችውን የፍፁም ቅጣት ምት አጥቂው ዲያዴ ዲያአንካ ወደ ጎልነት ለውጧት በማሊ 1-0 መሪነት የመጀመርያው አጋማሽ ሲጠናቀቅ ዲያዴ ዲአንካ በድጋሚ በጨዋታ በ82ኛው ደቂቃ ላይ ሁለተኛውን አክሏል። በጭማሪው ደቂቃ ላይ ደግሞ አሌይ ማሌ እና አብዱላይ ዲያቤ ተጨማሪ ግብ አክለው ጨዋታው 4-0 የተጠናቀቀ ሲሆን በድምሩ 5-1 በሆነ አጠቃላይ ውጤት ኢትዮጵያ ተሸንፋ ከማጣሪያው ውጪ ሆናለች፡፡

ማሊ በቀጣይ የማጣርያ ዙር ካሜሩንን የምትገጥም ይሆናል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *