ሊዲያ ታፈሰ ወደ ኳታር አምርታለች

በፈረንሳይ አስተናጋጅነት ለሚካሄደው የሴቶች የዓለም ዋንጫ ከአፍሪካ ከተመረጡት ዳኞች አንዷ የሆነችው ሊዲያ ታፈሰ ለመጨረሻ ፈተና ወደ ኳታር አቅንታለች፡፡
ያለፉትን ስድስት ዓመታት በአፍሪካ እና በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚሰናዱ ውድድሮችን እየመራች የምትገኘው ሊዲያ ታፈሰ ከፊቷ ለሚጠብቃት የዓለም የሴቶች ዋንጫ ከአፍሪካ ከተመረጡ ሶስት እንስት ዋና ዳኞች መሀል አንዷ ነች። በቅርቡ ወደ ኳታር እና ፖርቹጋል አምርታ ቅድመ ፈተናዎችን ያካሄደች ሲሆን በፖርቹጋል ከነበራት የፈተና እና ስልጠና በተጨማሪ የአሊጋርቭ ዋንጫ ጨዋታዎች ላይ መርታ ተመልሳለች፡፡

ትላንት በአዲስ አበባ ስታዲየም ከጉዞዋ በፊት የመጨረሻዋ የሆነውን ልምምድ በማድረግ ላይ ሳለች ከሶከር ኢትዮጵያ ጋር ቆይታ የነበራት ሊዲያ “ይህ ትልቅ ውድድር ነው። ሀገሬን ወክዬ እንደመጓዜ ብርቱ የሆነ ፈተና ይጠብቀኛል። ያን ለማድረግ ደግሞ ጠንክሬ ስሰራ ቆይቻለሁ።” ብላለች።

ሌሊት 7:00 ላይ የበረረችው ሊዲያ በኳታር ለአንድ ሳምንት ቆይታ የሚኖራት ሲሆን በዛ የሚደረገውን የአረብ ሀገራት ከ17 ዓመት በታች ዋንጫንም እንድትመራ ከመመረጧ ባሻገር የVAR አተገባበር ስልጠናም የምትወስድ ይሆናል፡፡


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *