በጅማ አባጅፋር ያለፉትን ስድስት ወራት ያሳለፈው ተከላካዩ ያሬድ ዘውድነህ ወደ ቀድሞ ክለቡ ድሬዳዋ ተመልሷል፡፡
በሁለተኛው የውድድር ዘመን አጋማሽ ጅማሮ በሜዳው ኢትዮጵያ ቡናን ከረታ በኋላ በደቡብ ፖሊስ ከሜዳው ውጪ ሽንፈት የገጠመው ድሬዳዋ ከተማ በሁለተኛው ዙር የዝውውር መስኮት ከቀላቀላቸው ምንያህል ተሾመ፣ ኤልያስ ማሞ እና ኤርሚያስ ኃይሉ በመቀጠል አራተኛ ተጫዋቹ የሆነው ያሬድ ዘውድነህን በአንድ ዓመት ውል አስፈርሟል፡፡
የመሀል እና መስመር ተከላካዩ ያሬድ በ2010 ወልዲያን በመልቀቅ ዳግም ድሬዳዋን መቀላቀሉ የሚታወስ ሲሆን ከአንድ የውድድር ዓመት በኋላ ወደ ቻምፒዮኖቹ ጅማ አባጅፋር በማምራት በአንድ ውል በክለቡ ለመቆየት የተስማማ ቢሆንም በክለቡ የመጀመሪያው ዙር የሊግ ውድድር እና የአፍሪካ መድረክ ጉዞ ላይ ተሳትፎን ካደረገ በኋላ የአራት ወራት ውል እየቀረው ክለቡን በመልቀቅ ወደ ድሬዳዋ ዳግም ተመልሷል፡፡
© ሶከር ኢትዮጵያ
በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡