በከፍተኛ ሊግ ግማሽ ዓመት የዝውውር መስኮት ላይ ክለቦች ያደረጉትን ተሳትፎ በከፊል እነሆ!
– የምድቡ መሪ ኢትዮጵያ መድን ሁለት ተጫዋቾችን ወደ ቡድኑ ቀላቅሏል። በደደቢት የግማሽ ዓመት ቆይታ የነበረው ያሬድ መሐመድ እንዲሁም ከቢሾፍቱ አውቶሞቲቭ ፀጋ ዓለማየሁ ወደ ቡድኑ የተቀላቀሉ ተጫዋቾች ናቸው።
ባለፈው ሳምንት አምስት ተጫዋቾች ያስፈረመው ወልቂጤ ከተማ አንድ ተጨማሪ ተጫዋች አስፈርሟል። ሲሳይ ቶላ የቡድኑ አዲስ ፈራሚ ነው።
– በደረጃ ሰንጠረዥ ወገብ ላይ የሚገኘው ናሽናል ሴሜንት የቀድሞ ተጫዋቹ እዮብ መስፍን ወደ ቡድኑ ሲቀላቅል ፈሪድ አድናን ከድሬዳዋ ተስፋ ቡድን፤ ፋይጠን አብዱራማን ድሬዳዋ ዲቪዝዮን እንዲሁም ማስረሻ አብርሃምን ከሀገረማርያም መቀላቀል ችሏል።
– ዋና አሰልጣኙን በአዲስ አሰልጣኝ የተካው ሀላባ ከተማ አብዱልከሪም ራህመቶ እና ማስረሻ ሙሉጌታን ከተስፋ ቡድኑ ሲያሳድግ ከዚህ ቀደም ከሀላባ ታዳጊ ቡድን ወደ ጅንካ የተዘዋወረው ግብ ጠባቂው አድነው አባተ ወደ ቡድኑ ቀላቅሏል።
– የደረጃ ሰንጠረዡ ግርጌ ላይ የሚገኘው የካ ክፍለ ከተማ በርካታ ተጫዋቾች ሲያስፈርም አብዱልሀፊዝ መኪ (አማራ ውሃ ስራ /ግብ ጠባቂ)፣ ብሩክ መስፍን (ሮቤ ከተማ)፣ ዮሐንስ አድማሴ (ሰበታ ከተማ )፣ ግርማ ዓለሙ እና ዳኛቸው አረጋ (ቤንች ማጂ ቡና)፣ እንዳለማው ድክሬ፣ ግሩም አንተነህ፣ ዳዊት ተፈራ፣ ማንደፍሮት ወ/ጊዮርጊስ (ከምባታ ሺንሽቾ)፣ ማቲያስ ሹመቴ (ቡራዩ ከተማ) ቡድኑን የተቀላቀሉት ተጫዋቾች ናቸው።
© ሶከር ኢትዮጵያ
በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡