በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ በምድብ ሀ ተደልድሎ ውድድሩን እያደረገ የሚገኘው አውስኮድ ከመፍረስ አደጋ መትረፉን ተከትሎ አዲስ አሰልጣኝ ቅጥር ሲፈፅም በ12ኛ ሳምንት ሊያደርገው የነበረው ተስተካካይ ጨዋታ ወደ ሌላ ጊዜ ተሸጋግሯል።
እንዳወቅ አጥናፉ አዲሱ የአውስድ አሰልጣኝ ናቸው። በዘንድሮው የውድድር ዓመት በጥረት የሴቶች ቡድን ውስጥ ሲሰሩ የቆዩት እንዳወቅ ከዚህ ቀደም በባህር ዳር ከተማ እና በባህር ዳር ዩንቨርሲቲ ሰርተው አልፎል። አሰልጣኙ ከሶከር ኢትዮጵያ ጋር በነበራቸው ቆይታ ” አሁን ላይ ዋና ሀሳባችን ቡድኑን ካለበት የደረጃ ሰንጠረዥ ግርጌ በማላቀቅ ከፍ ማድረግ ነው። የተወሰኑ ተጫዋቾች ከቡድኑ ጋር ባለመሆናቸው በነሱ ምትክ ለማምጣት ጥረት ላይ ነን። ” ብለዋል።
በተያያዘ ዜና የከፍተኛ ሊግ ኮሚቴ ሁሉም ቡድኖች እኩል ቁጥር ያለው ጨዋታ እንዲያከናውኑ በዚህ ሳምንት ከመደበኛው (13ኛ ሳምንት) ይልቅ በ12ኛ ሳምንት ሳይደረጉ የቀሩ ጨዋታዎች እንዲከናወኑ ቢወስንም በርካታ የቡድኑ ተጫዋቾችን ያጣው አውስኮድ ከፌዴራል ፖሊስ ጋር ያደርጋል ተብሎ የተጠበቀው ጨዋታ ወደ ሌላ ጊዜ ተላልፏል።
© ሶከር ኢትዮጵያ
በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡