አሰልጣኝ ዮሴፍ ተስፋዬ ያለፉትን አራት ቀናት ከ40 በላይ ለሆኑ ተጫዋቾች የመጀመርያ ጥሪ ካደረጉ በኋላ በትናትናው ዕለት የመጨረሻ 25 ተጫዋቾቻቸውን ለይተው አሳውቀዋል።
ከሚያዚያ 3 ጀምሮ በአራት ሀገራት መካከል በኤርትራ አስተናጋጅነት ለሚካሄደው “የሠላም እና የወዳጅነት ” ውድድር ተሳታፊ የሆነው የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ዝግጅቱን ጀምሯል። በቅርቡ የአሰልጣኝ ቅጥሩን ይፋ ከሆነበት ጊዜ ጀምሮ ዋና አሰልጣኝ ዮሴፍ ተስፋዬ እና እረዳቶቻቸው ከ40 በላይ ተጫዋቾችን የመጀመርያ ጥሪ ካደረጉ በኃላ ያለፉትን አራት ቀን ምልመላ ሲያደርጉ ቆይተው የመጨረሻ 25 ተጫዋቾችን ለይተዋል።
ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድኑ ሐራምቤ ሆቴል ጊዜያዊ ማረፊያውን በማድረግ ከትናትናው ጀምሮ መደበኛ ዝግጅታቸውን እያደረጉ ይገኛል።
የተጫዋቾቹ ስም ዝርዝር
ግብጠባቂዎች
ተመስገን ዮሐንስ (ቅዱስ ጊዮርጊስ)
አቡሽ አበበ (ወላይታ ድቻ)
ዳዊት ባህሩ (ኢትዮጵያ ቡና)
ተከላካዮች
ፉአድ ነስሩ (ኢትዮጵያ ቡና)
ያብስራ ሙልጌታ (ቅዱስ ጊዮርጊስ)
ሙአዝ ሙኡዲን (አዳማ ከተማ)
እዮብ ማቲዮስ (አዳማ ከተማ)
ቃላአብ ፍቅሩ (ኢትዮጵያ ቡና)
ሀጎስ ኃይሉ (መከላከያ)
አክሊሉ ዓለሙ (ኢትዮጵያ ቡና)
እያሱ ለገሰ (አአ ከተማ)
አማካዮች
ረድዋን ናስር (አአ ከተማ)
ብሩክ መንገሻ (አዳማ ከተማ)
ሙሴ ከበላ (ኢትዮጵያ ቡና)
ሉክ ፖሊኒሆ (ቅዱስ ጊዮርጊስ)
ቴዎድሮስ ገብረእግዚአብሔር (ቅዱስ ጊዮርጊስ)
ወንድማገኝ ኃይሉ (ሀዋሳ ከተማ)
አብዱልከሪም ወርቁ (ወልቂጤ ከተማ)
አጥቂዎች
በየነ ባንጃ (ኢትዮጵያ ቡና)
አላዛር ሽመልስ (አአ ከተማ)
መስፍን ታፈሰ (ሀዋሳ ከተማ)
ምንተስኖት እንድርያስ (ሀዋሳ ከተማ)
እዮብ አለማየሁ (ወላይታ ድቻ)
መሐመድ አበራ (መከላከያ)
ታምራት ስላስ (ወላይታ ድቻ)
© ሶከር ኢትዮጵያ
በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡