ሴካፋ 2015 ፡ ‹‹ጨዋታውን ማሸነፋችን ይገባናል›› አሰልጣኝ ዮሃንስ ሳህሌ

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ዛሬ በአዲስ አበባ ስታድየም ታንዛንያን በመለያ ምቶች አሸንፎ ወደ ግማሽ ፍፃሜው ተቀላቅሏል፡፡ ከጨዋታው በኋላ አስተያየታቸውን የሰጡት አሰልጣኝ ዮሃንስ ሳህሌ በሴካፋ 20 ተጫዋች ብቻ እንዲጠቀሙ መገደዳቸው ቡድናቸውን እንደጎዳው ተናግረዋል፡፡ አሰልጣኙ የሰጡትን አስተያየት እንዲህ አሰናድተነዋል፡፡

 

‹‹ጨዋታውን ማሸነፋችን ይገባናል››

‹‹ ጨዋታውን ማሸነፋች ይገባን እንደነበር አስባለሁ፡፡ ጨዋታውን በጊዜ (በመደበኛው ክፍለ ጊዜ) ለመጨረስ የሚስችሉ የግብ እድሎችን አልተጠቀምንባቸውም፡፡ ከባለፈው ጨዋታ ተሸሽለናል፡፡ እነሱም እንደ ቅዳሜው ጨዋታ አልበለጡንም፡፡››

 

እድል

‹‹ ግብ ጠባቂውን ጨምሮ አብዛኛዎቹ ተጫዋቾች ለብሄራዊ ቡድን የመጫወት ልምድን እዳበሩ ነው፡፡ ከቀን ወደ ቀን ቡድናችን እየተሸሻለ ነው፡፡ በራስ መተማመናቸውም እየዳበረ ነው፡፡ በእድል ነው እዚህ የደረሳችሁት ሚለውን አልቀበለውም፡፡ እድል የሚባለው አንድ ጊዜ ስታሸንፍ ነው፡፡ እዚህ ለመድረስ ግን ታግለናል፡፡ ››

 

የሴካፋ ህግ

‹‹ 4 ተጫዋቾችን በጉዳት አጥተን ነው ታንዛንያን የገጠምነው፡፡ ሴካፋ ለውድድሩ 20 ተጫዋች ብቻ መጠቀም እንደሚኖርብን የሚያስገድደውን ህግ እቃወማለሁ፡፡ ባሉት ተጫዋቾች በየ24 ሰአት ልዩነት መጫወት አስቸጋሪ ነው፡፡ ተጫዋቾች እየተጎዱ ጨዋታውም ውብ አይሆንም፡፡ በዛሬው ጨዋታ 7 ተጠባባቂ ተጫዋች መያዝ ሲገባን በጉዳት ምክንያት የያዝነው 5 ብቻ ነበር፡፡ በቀጣይ ጨዋታዎች ራምኬል እና ስዩም ከጉዳት ሲመለሱ ለኛ የተሻለ ይሆናል፡፡ ››

 

ስለ አጨዋወታቸው

‹‹ ከ24 ሰአት በፊት የተጫወትነውን ቡድን የገጠምነው፡፡ እንዴት እደምንጫወት ውቃሉ፡፡ እነሱ ጨዋታውን ደግመው እንደሚመለከቱት ሁሉ እናም ተመልክተነዋል፡፡ በዚህም ዛሬ አጨዋወታችንን ቀይረን ገብተናል፡፡ ባለፈው ጨዋታ በአማካይ ክፍሉ ብልቻ ተወስዶብን ነበር፡፡ ጋቶችም ከ3 ተጫዋቾች ጋር ይጋፈጥ ነበር፡፡በዚህ ጨዋታ ኤልያስ ማሞን አስገብተን የመሃል ሜዳ ብልጫ እንዳይወሰድብን አድርገናል፡፡ ጋቶችም ካለፈው ጨዋታ በተሻለ ጠቅሞናል፡፡ ››

ያጋሩ