ከቄራ እና አካባቢው ተነስተው በኢትዮጵያ እግርኳስ ታሪክ ውስጥ አሻራቸውን ጥለው ላለፉ ባለሙያዎች የሚታወሱበት ቋሚ የምስል ማሳያ ቢልቦርድ በአልማዝዬ ሜዳ ቆመላቸው።
ዛሬ በአልማዝዬ ሜዳ በርካታ የስፖርት ቤተሰቦች በታደሙበት በዚህ መርሐ ግብር ለማድመቂያ የፖሊስ ማርሽ ባንድ የተገኘ ሲሆን ጥሪ የተደረገላቸው የክብር እንግዶች የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ አብርሃም መብራቱ፣ የአአ አግርኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝደንት ኃይለኢየሱስ ፍስሐ እና ሌሎች እንግዶች ተገኝተዋል።
በቄራ እና በአካባቢው ተገኝተው በተለያዩ ዘመናት በኢትዮጵያ እግርኳስ ታሪክ ውስጥ አሻራቸውን አሳርፈው ያለፉ ባለሙያዎች በዚህ ቋሚ ምስክር በሆነው ቢልቦርድ ላይ ፎቷቸው በክብር ተሰቅሏል። የዕለቱ የክብር እንግዶች በክብር ፎቶቸው የተሰቀለውን ግለሰቦች እየዞሩ የጎበኙ ሲሆን በአዘጋጅ ኮሚቴው አማካኝነትም ገለፃ ተደርጎላቸዋል። ከክብር ፎቷቸው ከተሰቀሉ ግለሰቦች መካካል በቅርቡ በሞት የተለዩን የኢትዮጵያ እግርኳስ ባለውለታ የአሰልጣኝ ሥዩም አባተ አንዱ ናቸው።
© ሶከር ኢትዮጵያ
በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡