ሀዋሳ ከተማ እና ሲዳማ ቡና በቅርቡ ካስፈረሟቸው ተጫዋቾች ጋር ተለያይተዋል

ጋናዊ ተጫዋቾች ወደ ክለባቸው ያመጡት ሀዋሳ ከተማ እና ሲዳማ ቡና የወረቀት ጉዳዮች ባለመጠናቀቃቸው መለያየታቸው ታውቋል፡፡

በአጥቂ ስፍራ ላይ ከፍተኛ ክፍተት የሚታይበት ሀዋሳ ከተማ በቅርቡ ጋናዊውን አጥቂ ኩዋሜ አትራምን ወደ ክለቡ መቀላቀሉ ይታወሳል። በ2010 ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት ድሬዳዋ ከተማ መጫወት የቻለው አትራም ሀዋሳ ከተማ ከአንድ ወር በፊት የተቀላቀለ ቢሆንም ከነበረበት ክለብ የመልቀቂያ ወረቀት በጊዜ ባለመጠናቀቃቸው ምክንያት በክለቡ አንድም ጨዋታ ላይ መሰለፍ ሳይችል ከክለቡ ለመለያየት ተገዷል፡፡

ከ 20 ቀናት በላይ በሙከራ ካሳለፈ በኃላ በአንድ ዓመት የውል ኮንትራት ለሲዳማ ቡና መፈረም የቻለው ጋናዊው አልሀሰን ኑሁ እንደ አትራም ሁሉ ከቀድሞው ክለቡ ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን መድረስ የነበረበት ወረቀት በሰዓቱ ባለመድረሱ ምክክያት ምንም አይነት ጨዋታ ላይ መሳተፍ ሳይችል ክለቡን ለመልቀቅ ተገዷል፡፡


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡