በነቀምት ከተማ የሚገኘውና ከአስር ዓመት በላይ የግንባታ ጊዜ የፈጀው የወለጋ ስታዲየም ግንባታ ተጠናቀቀ።
ከሚሌንየሙ መባቻ አንስቶ የመሰረት ድንጋይ ተቀምጦለት በአጭር ጊዜ ውስጥ ግንባታው ተጠናቆ አገልግሎት ይሰጣል ተብሎ የታሰበው የወለጋ ስታዲየም ከዓመታት መዘግየት በኋላ ዛሬ ግንባታው ተጠናቆ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት በተገኙበት ተመርቋል።
ስታድየሙ 2004 ይጠናቀቃል ተብሎ ቢገመትም ከመጫወቻው ሜዳ ሳር ጥራት ጋር ተያይዞ ግንባታው ዘግይቶ የቆየ ሲሆን ከ200 ሚልዮን ብር በላይ የፈጀው ይህ ስታዲየም ዙርያው ሙሉ ለሙሉ ወንበር ባይገጠምለትም ከ50ሺህ በላይ ተመልካች የመያዝ አቅም እንዳለው ለማወቅ ችለናል።
በከፍተኛ ሊግ ምድብ ሐ ላይ ከመቼውም ዓመታት በተሻለ በጥንካሬ እየተጓዘ በሦስተኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው ነቀምት ከተማ በዚህ ስታዲየም እየተጫወተ እንደሚገኝ ይታወቃል።።
© ሶከር ኢትዮጵያ
በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡