ቅዱስ ጊዮርጊስ የውይይት መድረክ አዘጋጀ 

የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማኅበር ለሁለት ቀናት የሚቆይ በስፖርታዊ ጨዋነት ላይ ያተኮረ የውይይት መድረክ በሼራተን አዲስ አዘጋጅቷል።

ለሁለት ቀናት (ከሚያዚያ 14-15) የሚቆየው ይህን የውይይት መድረክ የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማኀበር ዋና አዘጋጅነት የሠላም ሚኒስቴር፣ ባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር እንዲሁም ኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን በተባበሪነት ነው ያዘጋጁት።

” የስፖርታዊ ጨዋነት ምንጮች ” በተሰኘው በዚህ የውይይት መድረክ ከፍተኛ የመንግስት አመራሮች በስፖርቱ የሚገኙ ባለ ድርሻ አካላት ይታደሙበታል ተብሎ ይጠበቃል። በተለያዩ ባለሙያዎች ጥናታዊ ፁሑፎች የሚቀርቡ ሲሆን በጉባዔው ተሳታፊዎችም መካከል የውይይት ጊዜ ሊኖር እንደሚችል ለማወቅ ችለናል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡