ሳላዲን ሰኢድ ለኤምሲ አልጀር የመጀመርያ ግቡን አስቆጠረ

ኢትዮጵያዊው አጥቂ ሳላዲን ሰዒድ በኤምሲ አልጀር ማልያ የመጀመሪያ ግቡን አስቆጥሯል፡፡ በክረምቱ የዝውውር መስኮት የግብፁን ታላቅ ክለብ አል አህሊ ለቆ የአልጄርውን ኤምሲ አልጀር ተቀላቀለው የብሄራዊ ቡድናችን አጥቂ በአዲሱ ክለቡ ከጉዳት ጋር በተያያዘ በርካታ ጨዋታዎችን ማድረግ አልቻለም፡፡

ከጉዳቱ በቅርቡ ያገገመው ሳላዲን ኤምሲ አልጀር አርሲ አርባን 2-1 ባሸነፈነበት የወዳጅነት ጨዋታ ነው ግብ ማስቆጠር የቻለው፡፡ ሳላ በውድድር ዘመኑ ለአልጀርሱ ክለብ በሊግ ጨዋታዎች ላይ ግብ አላስቆጠረም፡፡

ሳላዲን ከጉዳት መልስ ባሳለፍነው ሳምንት ኤምሲ አልጀር ከሲኤስ ኮንስታንታይን ጋር 1ለ1 በተለያየበት ጨዋታ በ59ኛው ደቂቃ ተቀይሮ መግባቱ የሚታወስ ነው፡፡

ያጋሩ